የኬንያው ፕሬዝዳንት ሩቶ የ #ኢትዮጵያ ህዳሴግድብ የምረቃ ስነ-ስርዓት “ዋና እንግዳይሆናሉ
አዲስ አበባ፣ ጳጉሜ 2፣ 2017 - የኬንያው ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ “የአፍሪካ ራስን መቻልና የኢትዮጵያ ወሳኝ ምዕራፍ” በማለት የገለጹት የታላቁ ህዳሴ ግድብ የምረቃ ስነ-ስርዓት “ዋና እንግዳ” እንደሚሆኑ ተገለጸ። የፕሬዝዳንቱ ጽህፈት ቤት ቃል አቀባይ በእሁድ ዕለት ባወጣው መግለጫ ላይ የፕሬዝዳንቱ መገኘት መረጋገጡን አስታውቋል።
ፕሬዝዳንት ሩቶ እና ልዑካቸው ዛሬ ጠዋት አዲስ አበባ ገብተዋል። ይፋ ያልሆኑ መረጃዎች እንደሚጠቁሙት ህዳሴ ግድብ ማክሰኞ ጳጉሜ 4፣ 2017 ይመረቃል።
የኬንያው ፕሬዝዳንት ጽህፈት ቤት የህዳሴ ግድብን ክልላዊ ጠቀሜታ አጉልቶ ሲገልጽ፣ በኢትዮጵያ እና በኬንያ መካከል ያለው የኃይል ማስተላለፊያ መስመር “ንፁህና ተመጣጣኝ ዋጋ ያለው ኤሌክትሪክ የሚያቀርብና የኃይል ደህንነትን የሚያጠናክር፣ በድርቅ ወቅት አቅርቦትን የሚያረጋጋ እና የኢንዱስትሪ ዕድገትን የሚደግፍ” ነው ብሏል። አያይዞም ይህ ፕሮጀክት ከኬንያ-ታንዛኒያ ማስተላለፊያ መስመር ጋር በመሆን በጋራ ታዳሽ ኃይል አማካይነት የምስራቅ አፍሪካን ውህደት እንደሚያሳድግ አስረድቷል።
Seledadotio

1 year ago