Logo
YenetaTube
የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ልዑክ ቡደን ዛሬ ማታ ሽኝት ይደረግለታል

በጃፓን ቶኪዮ ለሚካሄደው የዓለም ሻምፒዮና የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ልዑክ ቡድን ዝግጅቱን አጠናቋል ።

በዚህ መሠረት ዛሬ ጳጉሜ 1/2017 አመሻሽ 11:00 ላይ በስካይ ላይት ሆቴል ደማቅ ሽኝት ይደረግለታል።

ኢትዮጵያ በሻምፒዮናው የርምጃ ውድድርን ጨምሮ ከ800 ሜትር እስከ ማራቶን ባሉት ርቀቶች ትካፈላለች ።

በሽኝት መርሀግብሩ ላይ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች ፣ አምባሳደሮች ፣ የፌዴሬሽኑ የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላትና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ይገኛሉ።

20ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ከቅዳሜ መስከረም 3
እስከ እሁድ መስከረም 11/ 2018 ዓ.ም በጃፓን ቶኪዮ ይካሄዳል

Ethiopian Athletics Federation

1 year ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.