Logo
YenetaTube
ሩሲያ እና ቻይና በአለም ላይ ትልቁን የንግድ ልዉዉጥ ስምምነት ፈፀሙ !
‎
‎
‎የሩስያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን የሳይቤሪያ-2 ፓወር መስመር ዝርጋታ ሁለቱ ሀገራት ስምምነት ከተፈራረሙ በኋላ በሩሲያ እና በቻይና መካከል ያለውን ግንኙነት "ከዚህ በፊት ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ ከፍተኛ ደረጃ ላይ እንደሚገኝ" ገልፀዋል ሲል CNN ዘግቧል።
‎
‎ይህም የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ እየተጣለ የሚገኘው የታሪፍ እና ከጊዜ ወደ ጊዜ እያገለሉ የሚሄዱ ፖሊሲዎች በመቃረን የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ እና የአለም አቀፍ ንግድ አካሄድ ለውጥ የሚያመጣ የአለምን ስርዓት የሚቀይር ተብሏል ።
‎
‎ይህ ግዙፍ ፕሮጀክት በዓመት 50 ቢሊዮን ኪዩቢክ ሜትር የተፈጥሮ ጋዝን ከምእራብ ሩሲያ ወደ ሰሜናዊ ቻይና በሞንጎሊያ በኩል የሚያጓጉዝ ሲሆን የዩክሬን ጦርነት ከጀመረ በኋላ ሩሲያ ወደ አውሮፓ ከምትልከው የጠፋ ጋዝ ግማሹን ያካክላል ተብሎ ይጠበቃል።
‎
‎ማክሰኞ ከሰአት በኋላ ፣የሩሲያ የመንግስት ኢነርጂ ኩባንያ ጋዝፕሮም ሞስኮ ለዓመታት ሳትቀበለዉ የቆየችዉ ከአዉሮጳ ጋር ያላትን የንግድ ልዉዉጥ በመግፋት አዲስ የንግድ ልዉዉጥ ያለውን ግዙፍ የሳይቤሪያ-2 ጋዝ ቧንቧ መስመር ለመገንባት ሕጋዊ ስምምነት መፈረሙን አስታውቋል።
‎
‎ ሲ ኤን ኤን እንደዘገበው ይህ ስምምነቱ ፑቲን አውሮፓን በዋና ጋዝ ገዥነት ለመተካት ወደ ቻይና በማዞር ትልቅ ድል ነው። በተጨማሪም የዩኤስ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በዩክሬን ያለውን ጦርነት ለማስቆም ባደረጉት ጥረት የሩሲያን የሃይል አቅርቦት እንዲቀንሱ ሀገራትን ግፊት በማድረግ ላይ የሚገኙትን የጋራ ተቃውሞ ማሳያ ነው። ሲል ዘግቧል ።
‎
‎የቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ማክሰኞ በተደረገው መደበኛ የዜና ኮንፈረንስ ስለ ስምምነቱ ሲጠየቁ ቻይና እና ሩሲያ “ኃይልን ጨምሮ በተለያዩ መስኮች ያለማቋረጥ ተግባራዊ ትብብር አድርገዋል”ብለዋል ።
‎
‎የጋዝፕሮም ዋና ሥራ አስፈፃሚ አሌክሲ ሚለር እንደተናገሩት ስምምነቱ የ 30 ዓመት የአቅርቦት ስምምነትን ያካተተ ሲሆን የአቅርቦት ዋጋ አውሮፓ ከሚከፍለው ያነሰ ይሆናል ። "በአለም ላይ ትልቁ፣ በጣም ሰፊ እና ከፍተኛ ካፒታል-ተኮር የጋዝ ፕሮጀክት ይሆናል" ሲል ሚለር በ TASS የዜና ወኪል በኩል ተናግሯል ።
‎
‎ፑቲን ቻይናን በጎበኙበት ወቅት ሁለቱ መሪዎች ከሞንጎሊያው ፕሬዝዳንት ኡክና ክሩልሱክ ጋር በመገናኘት እና በቻይና መሪ ይፋዊ መኖሪያ ቤት ሻይ ሲጠጡ ለሰዓታት አብረው አሳልፈዋል።
‎
‎
‎የኔታ ቲዩብ ዘጋቢ ፦ ታዴ የማመይ ልጅ

1 year ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.