Logo
SeledaPost
"የኢትዮ-ኤርትራ ጦርነት ከተጀመረ ኤርትራ አሰብን ማጣቷ የማይቀር ነው''

አንጋፋው ፖለቲከኛ አቶ በረከት ስምኦን መቀመጫውን አሜሪካ አገር ላደረገ ኢትዮ ሪቪው ለተባለ ድህረገጽ አነጋጋሪ አስተያየት ሰጥተዋል ። ከለውጡ በፊት ትልቅ ሚና የነበራቸው አቶ በረከት ስለ ኢትዮ ኤርትራ እና ስለ ህወሓት ቤት ስለ ተፈጠረው ሹኹቻ ዙሪያ የሰጡት ትንታኔ ትኩረትን ስቧል ።

አቶ በረከት በኢትዮጵያና በኤርትራ መካከል የተፈጠረውን ውጥረት መሰረት አድርገው እንደተናገሩት ፤ የኢትዮ ኤርትራ ጦርነት ከተጀመረ እንደ ሩሲያ ዩክሬን ጦርነት ወደ ግዛት ልውውጥ መሄዱ የማይቀር ነው ።

በተለይ የሁለቱ ሀገራት ጦርነት ከተጀመረ ኤርትራ አሰብን ማጣቷ የማይቀር መሆኑን ገልጸዋል ። ይህ የተፈራው ጦርነት ከተቀሰቀሰ አስመራ ጫፍ ደርሶ አይቆምም፤ የኤርትራ ሉዐላዊነት ያበቃለታል ብለዋል ።

አቶ በረከት እንዳሉት ፤ጦርነት ከመጀመሩ በፊት የሻዕቢያ ስርዓት ከተገረሰሰ በኋላ በኤርትራ ሊፈጠር የሚችለውን ነገር መጀመሪያ ማሰላሰል መቅደም አለበት። በህወሓት እና በኤርትራ መካከል የተፈጠረው ግንኙነት ከሁሉም አቅጣጫ መዘጋት የለብንም የሚል የተስፋ እርምጃ ነው ።

ግን የህወሓት አመራሮች ኢሳይያስ አፈወርቂ በዓለም ደረጃ የተጠሉ መሪ መሆናቸውን የዘነጉ ይመስለኛል ። ህወሓት ከዚህ በኋላ ልታደስም ቢል የመታደስ ግዜው ያለፈ መስሎ ነው የሚታየኝ ነው ያሉት ።

አቶ በረከት የቀድሞው ጠ/ሚ ሀይለማርያም ደሳለኝንም ወቅሷል ጥሩ ጅማሮና ማበብ ላይ የነበረውን የደቡቡን ፖለቲካ እንዲፈርስ አድርጓል ሲሉ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል ። የአንጋፋውን ፖለቲከኛ አቶ በረከትን ስምኦን አስተያየት እንዴት እያችሁት?! ሃሳባችሁን አካፍሉን!!

Seledadotio
Seledadotio
1 year ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.