ዓለም ከኒውክሌር የጦር መሳሪያ ትፅዳ! /ጃፓን /
ሂሮሽማ እና ናጋሳኪ በተባሉ ከተሞቿ ላይ የአሜሪካ አዉቶም ቦንቦች ባዘነቡት መአት 200 ሺህ በላይ ህዝብ ያጣችው ዛሬም ጠባሳው ያልለቀቃት ጃፓን የሂሮሺማን የአቶሚክ ቦምብ ጥቃት 80ኛ ዓመት መታሰቢያ ባሰበችበት በዛሬው እለት በእኔ ይብቃ ስትል አለም ከኒውክሌር የጦር መሳሪያ የፀዳች እንድትሆን ጥሪ አቅርባለች።
ከአሜሪካ እስከ አውሮፓ፣ ቻይና እና ጃፓን ድረስ ወታደራዊ ወጪው እየጨመረ በመጣው የትጥቅ አዙሪት እና አዲስ ግጭቶች ለተወጠረችዉ አለማችን ኃይለኛ የጦር መሳሪያ አምራቾች በሁሉም የአለም ክፍሎች ውስጥ ካዝናቸውን መሙላት ይበቃል ያለችው ጃፓን "የሰው ልጅ በኒውክሌር ጦር መሳሪያ እራሱን አያጠፋው! ከኑክሌር ጦር መሳሪያ እና ከጦርነት በጸዳ አለም ውስጥ ለአንድ ሰው ማህበረሰብ በጋራ እንስራ!" ስትል ተደምጣለች ።
የጃፓን ጠቅላይ ሚኒስትር ሺገሩ ኢሺባ በሂሮሺማ የሰላም መታሰቢያ ፓርክ በተካሄደው ሥነ ሥርዓት ላይ ጃፓን በጦርነት ወቅት የአቶሚክ ቦምብ ጥቃት የደረሰባት ብቸኛዋ ሀገር መሆኗን አውስተው፤ ሀገራቸው የኒውክሌር ጦር መሣሪያን ለመግታት ያላትን ቁርጠኝነት ገልፀዋል።
"የሂሮሺማ የሰላም መታሰቢያ ሙዚየምን በጎበኘሁበት ወቅት እነዛን ከባድ ፈተናዎች እና ትዝታዎች እንዳይጠፉ እና ታሪክ ለትውልድ እንዲተላለፍ ቆርጯለሁ" ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ተናግረዋል።
በዘንድሮው 80ኛ ዓመት የመታሰቢያ በዓል ሥነ-ሥርዓት ላይ ከዓለም ዙሪያ የተሰባሰቡ ባለስልጣናትን ጨምሮ 55 ሺህ በላይ ሰዎች መገኘታቸውን አናዶሉ ዘግቧል።
ከ80 ዓመታት በፊት በሁለተኛው የዓለም ጦርነት 1937 ዓ.ም አሜሪካ በጃፓኗ ሂሮሺማ ከተማ ላይ በፈጸመችው የአቶሚክ ቦምብ ጥቃት ሙሉ ከተማዋ ወደ ፍርስራሽ የተቀየሩባት ጃፓን በአሁኑ ወቅት የአቶም ቦንብ ያላቻቸውና አለያም ቁልፍን በእጃቸው የማስገባት አቅም እያደራጁ የሚገኙትን በሙሉ ምድርን እንዳናጠፋ ኒኩሊየር "ከሰላም የሚያርቀን" ስለሆነ ይብቃ ብላለች ።
በቢዝነስ ኢንሳይደር ጃፓን ቱደይ ዘኢኮኖሚስት ምንጮቻችን ናቸዉ ።
የኔታ ቲዩብ ዘጋቢ ፦ ታዴ የማመይ ልጅ

1 year ago