Logo
Getu Temesgen
የመጽሐፍ ምረቃ
#ethiopia | የሌ/ኮሎኔል ታደሰ ሸዋቀና ገድሌ የሕይወት ታሪክ ~ ለሀገረ እና ለሕዝብ የተከፈለ መስዋዕትነት ~
ሰኞ፣ ሐምሌ 28 ቀን 2017ዓ.ም በኢትዮጰያ ብሔራዊ ቴአትር ይመረቃል።

ጌትነት እንየው

ዘነበ ወላ

ሥዩም ተፈራ

ፀጋዬ እሸቱ

ዕንቁ ዜማ

ሰለሞን ሙሄ

ደረጄ ኃይሌ / ኮሜዲያን/ በክብር ይጠብቋችኋል።

***
ለልጆቼ የማወርሳቸው

ለልጆቼ የማወርሳቸው ሀብት ስለሌለኝ የማወርሳቸው ታሪኬን ነው

ማንም ሰው አላፊ ነው፡፡ የእኔ የሕይወት መጨረሻ ጊዜ ልጆቼ «አባታችን እንደዚህ ያለ ታሪክ ነበረው» ብለው እንዲያስታውሱኝ ታሪኬን ጽፌላቸዋለሁ፡፡ ይህንንም ልምድ ወስደው ከእኔ የበለጠ ታሪክ ሠርተውና ታሪካንቸውን ጽፈው ለልጆቻቸው እንዲያስተ ላልፉ እመኛለሁ:: ያሁሉ ችግርና ፈተና አልፎ በአሁኑ ጊዜ አንዳችም ስሜት ሳይሰጠኝና ሳልበሣጭ ፈጣሪዬን እያመሰገንሁ በሠላም እየኖርኩ ሲሆን፡፡ ለእግዚአብሔር ምስጋና ይግባውና የ7 ልጆች አባትና 18 የልጅ ልጆች ለማየት በቅቻለሁ ገና ምን ታውቆ ይጨመር ይሆናል!

የኔ የመጨረሻ የሥራ ዕድል ደግሞ ከመሸ በኋላ ሁሉም ነገርበተመቻቸበት በሚድሮክ ለገደንቢ ወርቅ ማዕድን ኩባንያ በሕግ ሙያ ተቀጥሬ ዱሮ በሌ/ኮሎኔልነት ማዕረግ ከማገኘው ደመወዝ በላይ እየተከፈለኝ በሠላምና በደስታ እየሠራሁ 14 ዓመት በቅንነት እና በታማኝነት አገልግዬ ማረፍ ስለፈለኩ በራሴ አቤቱታ እንደ እ.ኢ.አ አቆጣጠር ከ1/1/2014 ዓ.ም. ጀምሮ ጡረታዬን አስከብሬያለሁ፡፡

***
+251 51 125788
+251 90 427270

1 year ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.