Logo
FastMereja
የሞሳድ ኃላፊ የጋዛ ነዋሪዎችን ወደ ኢትዮጵያ፣ ሊቢያና ኢንዶኔዥያ ለማዘዋወር አሜሪካ ድጋፍ እንድታደርግ መጠየቃቸው ተዘግበ

የእስራኤል የስለላ ድርጅት (ሞሳድ) ኃላፊ ዴቪድ ባርኔያ የጋዛ ነዋሪዎችን ወደ ኢትዮጵያ፣ ሊቢያ፣ ኢንዶኔዥያ ለማዘዋወር አሜሪካ ድጋፍ እንድታደርግ የሀገሪቱን ልዩ መልዕክተኛ መጠየቃቸው ተዘግበ።

የሞሳድ ኃላፊው ይህን ጥያቄ ያቀረቡት በዚህ ሳምንት በዋሽንግተን ባደረጉት ጎብኝት ወቅት መሆኑን አክሲዮስ ዘግቧል።

እስራኤል ፍልስጤማውያንን ከጋዛ ለማዘዋወር የትራምፕን አስተዳደር እርዳታ እየፈለገች መሆኑን ጉዳዩን የሚያውቁ ሁለት ምንጮችን ጠቅሶ የዜና አውታሩ ዘግቧል፣

ሁለቱ ምንጮች እንደገለፁት፤ የሞሳዱ ኃላፊ ባርኔያ፤ ኢትዮጵያ፣ ኢንዶኔዥያ እና ሊቢያ ከጋዛ የፍልስጤማውያን ስደተኞችን ለመቀበል ፈቃደኝነት አሳይተዋል ሲሉ ለአሜሪካ ልዩ መልዕክተኛ ስቲቭ ዊትኮፍ ተናግረዋል። እናም ዋሽንግተን እነዚህ ሀገራት ስደተኞችን ለማዛወር እንዲስማሙ “ማበረታቻ” መስጠት አለባት ማለታቸው ተገልጿል።

ይሁን እንጂ ስቲቭ ዊትኮፍ በጉዳዩ ላይ ቁርጠኛ አልነበረም ሲሉ አንደኛው ምንጭ ገልጿል።

የአሜሪካ ባለስልጣናትም ከአረብ ከሀገራት ተቃውሞ የሚያከትል በመሆኑ ዋይት ሀውስ ፍልስጤማውያንን ከጋዛ የማስወጣት ፍላጎት እንደሌለው ገልጸዋል ሲል ዘገባው አክሏል።

ከወራት በፊት የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የጋዛ ሰርጥ ግንባት ሲጀመር የጋዛ ነዋሪዎች በሙሉ ላልተወሰነ ጊዜ ወደሌላ ቦታ እንዲዘዋወሩ ሀሳብ ማቅረባቸው ይታወቃል። ሀሳቡን የእራኤሉ መሪ ኔታንያሁ እና ጥምረታቸው ሲደግፉ፣ የአረብ ሀገራት እና አብዛኛው የምዕራቡ ዓለም በብርቱ ተቃውመውታል።

ዘገባው የአዲስ ስታንዳርድ ነው

1 year ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.