#saudiarabia : በሳውዲ አረቢያ ዋና ከተማ ሪያድ በሚገኘው የንጉሥ ካሊድ ዓለም አውሮፕላን ማረፊያ ላይ በየመን " ሁቲ ታጣቂ ኃይል " በተፈጸመ ከባድ የሚሳይል ጥቃት 12 ሰዎች ሲሞቱ በመቶዎች ከሚቆጠሩ ሰዎች ቆስለዋል።
ሟቾቹ ፦
4 የሳዑዲ አረቢያ
2 የባንግላዴሽ
1 የአሜሪካ
1 የግብፅ
1 የጆርዳን
1 የሶሪያ
✌️ 1 የፍልስጤም
1 የሱዳን ዜጋ ናቸው።
የሳውዲ የሲቪል አቪዬሽን ባለሥልጣን ጥቃቱን ተከትሎ በአየር ማረፊያው ላይ የነበረው የበረራ እንቅስቃሴ በጊዜያዊነት መቋረጡን አስታውቋል።
በተመሳሳይ በዳማም በሚገኘው ንጉሥ ፋህድ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ አቅራቢያ የሚሳይል/ተወንጫፊ አካል ወድቋል። የሰው ህይወት አላለፈም፤ ጉዳትም አልደረሰም ተብሏል።
ባለፉት ጥቂት ቀናት ውስጥ (ረቡዕ እና ሐሙስ) በተመሳሳይ በዚሁ ኤርፖርት እና በሌሎች ኢላማዎች ላይ ተከታታይ ጥቃቶች ተፈጽመው ወደ 6 ሰዎች ተገድለዋል። ከሟቾቹ አንዱ ፓይለት ሲሆን የሳውዲ አየር መንገድ አውሮፕላን ተመቶ ነው ህይወቱ ያለፈው።
ሁቲዎች ለምን ጥቃት ይፈጽማሉ ?
በኢራን የሚደገፉትና የሚታጠቁት የሁቲ ኃይሎች ሳዑዲ አረቢያ እና አጋሮቿ በየመን ውስጥ በቁጥጥራቸው ስር ባሉ አካባቢዎች ላይ አዲስ እና የተጠናከረ ወታደራዊ ዘመቻ እንዲሁም የአየር ድብደባዎችን መክፈታቸውን በመቃወም አጸፋ እየመለሱ መሆኑን ነው የሚገልጹት። በተለይ ሳዑዲ ለየመን መንግስት በምትሰጠው ድጋፍ ጭምር ነው በሁቲ የድሮንና ሚሳኤል ጥቃት እየተፈጸመባት የሚገኘው።
ሳዑዲ አረቢያ ለምን ሁቲዎችን ታጠቃለች ?
ሳዑዲ አረቢያ በቅርቡ በየመን በኩል የሚገኘውን እና ለዓለም አቀፍ የንግድ መርከቦች ወሳኝ የሆነውን የባብ አል-መንደብ የባህር ወሽመጥ ከሁቲዎች ነፃ ለማውጣትና ዓለም አቀፍ እውቅና ያለውን መንግስት ለመደገፍ አብራ ከየመን መንግስት ጋር ዘመቻ ጀምራለች። ይህ ሰፊ የጋራ ወታደራዊ ዘመቻ የአየር ድብደባን ያከተተ ነው። ከዚህ ባለፈ ሁቲዎች እየፈጸሙባት ላለው ጥቃት ምላሽ ለመስጠት ነው።
ቪድዮ ፦ ማኅበራዊ ሚዲያ
ጥቅምት 1 ቀን 2019 ዓ/ም
@tikvahethiopia ቀይ ባህር ላይ ሁለት ግዙፍ የነዳጅ መርከቦች በሁቲ ማስጠንቀቂያ ጉዟቸውን ቀየሩ። ከሳዑዲ አረቢያ ነዳጅ ጭነው በቀይ ባሕር በኩል ሲቀዝፉ የነበሩ ሁለት ግዙፍ መርከቦች ከየመን ሁቲ ኃይሎች በተሰጣቸው ማስጠንቀቂያ ምክንያት አቅጣጫቸውን እንዲቀይሩ መደረጋቸው ተዘገበ። የሳዑዲን የነዳጅ ምርት ጭነው ወደ ቻይና እና ሕንድ ሲጓዙ የነበሩት ሁለቱ መርከቦች ወደ መጡበት የተመለሱት ሁቲዎች በሳዑዲ አረቢያ ላይ…

1 day ago