ከንግግር ባለፈ በተጨባጭ ፕሮጀክቶች የሚረጋገጥ የብልጽግና ጉዞ
አዲስ አበባ፣ መስከረም 30፣2019 (ኤፍ ኤም ሲ) ኢትዮጵያ ታሪካዊ የእድገት ምዕራፍ ላይ ትገኛለች። የኢትዮጵያ የመነሳት ዘመን በቃል ደረጃ የሚገለጽ የፖለቲካ መፈክር ሳይሆን በመሬት ላይ በሚታዩ ዘላቂና ግዙፍ ፕሮጀክቶች የሚረጋገጥ ሀገራዊ እውነታ ሆኗል።
ሀገሪቱ ለዘመናት የገባችበትን የጥሬ ዕቃ ኤክስፖርት ጥገኝነት በመስበር አዲስ የኢንዱስትሪና የኢኮኖሚ መዋቅር የመገንባት ስትራቴጂ በስፋት እየተተገበረ ይገኛል። በዛሬው ዕለት የተመረቀው ብሔራዊ የውድ ማዕድናት ማጣሪያ ፋብሪካም የዚህ ታላቅ አገራዊ ርዕይ አካል ነው።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በምረቃው ወቅት እንደገለጹት÷ በማዳበሪያ ፋብሪካ የጀመርነውን ሥራ በወርቅ ማጣሪያ ደግመነዋል፤ በሌሎችም ዘርፎች እንዲህ ዓይነት ሥራዎችን በመስራት ኢትዮጵያ በሚቀጥሉት 5 እና 10 ዓመታት ጥሬ ልኮ የበሰለ መቀበልን ታቆማለ ብለዋል።
ይህ ስኬት ሀገራችን ተፈጥሮአዊ ሀብቶቿን እሴት ጨምራ ለዓለም ገበያ ለማቅረብ ያላትን ቁርጠኝነት ያሳያል።
ይህ እሴት የመጨመር ጉዞ በወርቅና በማዳበሪያ ዘርፍ ብቻ የሚገደብ ሳይሆን በሌሎች ቁልፍ የኢኮኖሚ መስኮችም ሊደገምና ሊሰፋ የሚገባው መዋቅራዊ ሽግግር ነው።
በግብርናው ዘርፍ ሀገሪቱ የምታመርታቸውን እንደ ቡና፣ ሰሊጥና የቅባት እህሎች ያሉ ጥሬ ምርቶች በሀገር ውስጥ የማቀናበር ሥራ አጠናክሮ መሥራት አስፈላጊ ነው።
በተመሳሳይ በጨርቃጨርቅና አልባሳት ዘርፍ የተፈጥሮ ጥጥን በጥሬው ከመላክ ይልቅ በሀገር ውስጥ ፋብሪካዎች ፈትሎና አልብሶ ለውጭ ገበያ ማቅረብ ይገባል።
ኢትዮጵያ ያቀደችውን የብልጽግና ጉዞ እውን ለማድረግ የተጀመሩት ሀገራዊ ፕሮጀክቶች አዎንታዊ ውጤት እያመጡ ይገኛሉ።
ጥሬ ዕቃዎችን ብቻ ከመላክ ተላቃ እሴት የተጨመረባቸውን ምርቶች ወደ ዓለም ገበያ የማቅረብ ሂደቱ ተጠናክሮ ሲቀጥል ደግሞ ኢትዮጵያ አህጉራዊና ዓለም አቀፋዊ ተወዳዳሪነቷን በማረጋገጥ የጀመረችውን የብልጽግና ግብ በጽኑ መሠረት ላይ እንድታቆም ያስችላልታል።
በዮናስ ጌትነት

13 hours ago