Logo
TIKVAH-ETHIOPIA
እናት ፓርቲ መምህር ዮሐንስ ሸዋቀናን ፕሬዚዳንት ፤ ወ/ሮ ጥሩማር አባተን ም/ፕሬዚዳንት አድርጎ መረጠ።

2ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔውን በሶራምባ ሆቴል ዛሬ ያካሄደው እናት ፓርቲ፣ የሥራ አስፈጻሚ እና የላዕላይ ምክር ቤት አመራሮች ሹመት አካሂዷል።

በዚህም፥ መ/ር ዮሐንስ ሸዋቀና እና ኢ/ር በለጠ እያዩ የፓርቲው ፕሬዚዳንት ዕጩ ሆነው ቀርበው፣ መምህር ዮሐንንስ ፕሬዜዳንት ሆነው ተመርጠዋል።

ወ/ሮ ጥሩማር አባተ እና ሐብታም ግለጠው ደግሞ በም/ፕሬዚዳንት ዕጩ ሆነው ቀርበው፣ ወ/ሮ ጥሩማር ምክትል ፕሬዚዳንት ሆነዋል።

እንዲሁም
- አቶ ጥበቡ ይርጋ (ጠቅላይ ፀሐፊ)
- ወ/ሮ ሊባኖስ ደምሴ (ሕዝብ ግንኙነት)
- አቶ አያሌው ተስፋዬ (አባላት ምልመላ)
- አቶ አንዳርጌ መኹሪያ (የፖለቲካ ትንተና ክፍል)
- አቶ መኮንን ከበደ (የውጭ ግንኙነት ክፍል)
- ወ/ሮ ሐብታም ዳኘው (የመረጃ ግንኙነትና ቴክኖሎጂ ክፍል)
- አቶ ቴዎድሮስ በየነ (ፋይንስና እና ገቢ ማሰባሰቢያ ክፍል)
-ስመኝ ታደመ (ስልጠና እና አቅም ግንባታ ክፍል)
- አቶ ከፍያለው ዘውዱ (ፖሊሲና ምርምር፣ እቅድ ክፍል)
- ብርሃኑ ታዬ (የአካል ጉዳተኞች ክፍል)
- ወ/ሮ ሰብለወርቅ ፅጌ (ሴቶች እና ወጣቶች ክፍል)
- አቶ ዋለልኝ አስፋው (የሕግ እና ስነስርዓት ኮሚቴ)
- አቶ ሽመልስ ተገኝ (ሒሳብ ክዋኔ ኮሚሽን)
- መምህር መንግስቱ አረጋኸኝን (አርትኦት ኤዲትሪያል ቦርድ ኃላፊ) አድርጎ መርጧል።

ምልዓተ ጉባዔው ባለመሟላቱ ጠዋት 2 ሰዓት ይጀመራል ተብሎ ሲጠበቅ የነበረው ፕሮግራም የተጀመረው ከቀኑ 6 ሰዓት ነው። ከከሰዓት 11 ሰዓት ያልቃል የተባለው ጠቅላላ ጉባዔው የተጠናቀቀው ምሽት 3 ሰዓት ገደማ ነው።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሂደቱን ሲታዘብ መዋሉን እንደነበር ቲክቫህ ኢትዮጵያ አስተውሏል።

ከነጻነትና እኩልነት ፓርቲ ሲሳይ ነጋሽ፣ ከኢትዮጵያ ሶሻል ዲሞክራቲክ ፓርቲ (ኢሶዴፓ) ራሔል ባፌ፣ ከኢትዮጵያ ሕዝባዊ አብዮታዊ ፓርቲ (ኢሕአፓ) ምስጢረስላሴ ታምራት እና ሌሎችም ተገኝተዋል።

የእናት ፓርቲው ምክትል ፕሬዜዳንት አቶ ጌትነት ወርቁ በቅርቡ "ይብቃኝ" በሚል ከፖለቲካው ዓለም ማግለላቸው የሚታወስ ነው።

የፓርቲው ፕሬዚዳንት አቶ ሰይፈሥላሴ አያሌው ደግሞ "ከሀገር ወጥተዋል" የተባለ ሲሆን፣ የፓርቲውን 2ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔ በተመለከተ ዛሬ በዙም ገለጻ ሲያርጉ ቲክቫህ ኢትዮጵያ አስተውሏል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
መስከረም 30 ቀን 2019 ዓ/ም

@tikvahethiopia
7 hours ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.