Logo
YenetaTube
አሜሪካ እጆቿን ካልሰበሰበች ዩክሬን ላይ መአት ይወርዳል ! / ሞስኮ /

ሩሲያ ቅዳሜ እለት በአንድ ሌሊት ከ620 በላይ ሰው አልባ አውሮፕላኖችን እና የረዥም ርቀት ሚሳኤሎችን በመተኮሷ አራት ሰዎችን መግደሏን ያሳወቀችዉ ዩክሬን በሞስኮ ላይ አዲስ ማዕቀብ እንዲጣልባት መጠየቋ ተነግሯል ።

ዘሌንስኪ እንዳሉት ጥቃቱ በምዕራብ እና በደቡባዊ ግንባር ርቆ በሚገኘው በቼርኒቪትሲ ውስጥ መፈፀሙን የገለፁ ሲሆን ቢያንስ ሁለት ሰዎችን ሲገድል እና 20 ቆስሏል ። ብለዋል

የሩስያ መከላከያ ሚኒስቴር እንዳሳወቀው ባለፉት ቀናት ብቻ በምእራብ ፣ በምስራቅ ፣ በዲኒፕሮፔትሮቭስክ በላቪቭ፣ ካርኪቭ እና ሉትስክ በሚገኘው የዩክሬን ወታደራዊ-ኢንዱስትሪ ኮምፕሌክስ እና ወታደራዊ ኤሮድሮም ላይ ባሉ ኩባንያዎች ላይ ኢላማ ያደረጉ ጥቃቶችን መፈፀሙን አሳዉቋል ።

በሌላ በኩል የአየር ላይ ጥቃቶችን ከመቼዉም ጊዜ በላይ በጨመሩበት በዚህ ወቅት የዩናይትድ ስቴትስ ልዩ መልዕክተኛ ኪት ኬሎግ ዩክሬን ለመጎብኘት ማሰባቸውን ተከትሎ ሩሲያ አቋሟን ገልፃለች ።

አሜሪካ በዩክሬን በኩል ሞስኮን ለመክበብ የመስፋፋት ሃሳቧን እስከወዲያኛው ማሰብ እስካልተወች እና ለኬብ የምታደርገውን የመሳርያ ድጋፍ እስካላቆመች ድረስ ሩሲያ ካለፈዉ በጠነከረ መልኩ ማጥቃቷን እንደምትቀጥል እያሳወቀች ይገኛል ።

የሩሲያ የፀጥታው ምክር ቤት ምክትል ሊቀመንበር ዲሚትሪ ሜድቬዴቭ "ፕሬዚደንት ዶናልድ ትራምፕ ስለ ሩሲያ ያላቸዉን አመለካከትና እና የጦር መሳሪያ ጭነቶች ወደ ዩክሬን መላክ እስከቀጠለች ድረስ በዩክሬን ላይ የሚሳኤል መአት ማዉረዳችን እንቀጥላለን ሶስተኛው የአለም ጦርነት ቢጀመርም ግድ የለንም ። ብለዋል ።

ሞስኮ የዋሽንግተን ፖሊሲዎች ምንም ይሁን ምን የኔቶ መስፋፋት ሃሳብ እስኪያከትም ወታደራዊ አላማዋን መከተሏን ትቀጥላለች ሲሉ በቴሌግራም ቻናላቸዉ በኩል አቋማቸውን ጽፈዋል።

ትራምፕስ ለዩክሬን የጦር መሳርያ ድጋፍ ለማድረግ ማረጋገጣቸውን ተከትሎ አሜሪካ የቀጠናውን ሰላም እንደማትፈልግና ዩክሬን ከምድረ ገፅ እንድትጠፋ እየሰራች እንደሆነ በመጥቀስ የእርዳታውን ቃል ተችቷል።

ለዩክሬን ወታደራዊ ዕርዳታ በሰጡ ቁጥር ሩሲያ እስካሁን ያልተጠቀመቻቸዉን መሳርያዎች ለመጠቀም እንደምትገደድ የተናገሩት ሜድቬዴቭ እንዲህ ያሉት እርምጃዎች ጦርነቱን እንደሚያራዝሙት እና ወደ ሶስተኛው የአለም ጦርነት እንዳይገፉት አስጠንቅቀዋል ። ያለዉ ሞስኮ ታይምስ ነዉ ።

1 year ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.