ዲጂታል ኢትዮጵያ፡ ወደ ሀገራዊ የቴክኖሎጂ ሉዓላዊነት
አዲስ አበባ፣ መስከረም 29፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) ኢትዮጵያ በዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 ስትራቴጂ በቴሌኮም፣ በፋይዳ ብሔራዊ መታወቂያ እና በዲጂታል ክፍያዎች ያስመዘገበችውን ስኬት መሠረት በማድረግ፣ በ“ዲጂታል ኢትዮጵያ 2030” ወደ አዲስ የቴክኖሎጂ ምዕራፍ ተሸጋግራለች።
የዚህ ሀገራዊ ሽግግር ዋና ሞተር የወጣቶች ንቁ ተሳትፎ ነው።
በተለይም የ5 ሚሊየን ኢትዮ ኮደርስ ብሔራዊ ኢኒሼቲቭ ወጣቶችን በዌብ ፕሮግራሚንግ፣ ዳታ ሳይንስ፣ ሞባይል መተግበሪያ እና ሰው ሰራሽ አስተውሎት ማሰልጠን ተችሏል።
ይህም ወጣቶች በዓለም አቀፍ ገበያ ተወዳዳሪ በመሆን የውጭ ምንዛሬ እንዲያስገኙ አቅም ፈጥሯል።
ከሶፍትዌር ልማት ባሻገር፣ ቴክኖሎጂን በሀገር ውስጥ በማምረት የሃርድዌር ዘርፉን ማጠናከር፣ ጠንካራ የሳይበር ደህንነት ፖሊሲዎችን መቅረጽ እና የመከላከያ ሳይበር ማዕከልን መገንባት ለአስተማማኝ ዲጂታል ሥነ-ምህዳር መሠረት ጥለዋል።
7ኛው ጠቅላላ ሀገራዊ ምርጫ በስኬት መጠናቀቁን ተከትሎ የተመሠረተው አዲሱ የመደመር መንግሥት፣ ሀገሪቱን ከቴክኖሎጂ ተጠቃሚነት ወደ አምራችነት የማሸጋገርን የ2030 ራዕይ ዕውን ለማድረግ ትልቅ ምዕራፍ ይሆናል።
#የመደመር_መንግሥት

13 hours ago