Logo
Getu Temesgen
ሳያት ደምሴ
#ethiopia | እጅግ ሲበዛ ማንበብ ትወዳለች። አብዝታ ልታይ ልታይ አትልም። በቅርብ የሚያውቋት ከሷ በላይ ስለእርሷ ምስክር ናቸው።የበዛ ውጣ ውረድን በህይወቷ አሳልፋለች። የፅናት ተምሳሌት ናት።

የብዙ ሙያዎች ባለቤትም ናት። አንደበቷ ከማር ይጣፍጣል። ተናግራ ማሳመን ተክናበታለች። ለብዙ ሴት እንስቶች ሮል ሞዴል መሆን የምትችል ነች። የመጀመሪያ ሙያዋ ለሞዴልነት ነበር። በእሱም ጥሩ የሚባል ደረጃ ስኬት አግኝታበታለች። ገፍታ ባታስኬደውም ብዙ ውድድሮች አሸንፋለች። የሷ ልብ ግን ወደ ኪነጥቡ ያዘነበለ ስለነበር ብዙም ሳትቆይ ወደ ፊልሙ አለም ተቀላቀለች።
#ላውንደሪቦይ ላይ ምርጥ አርጋ ተውናለች ብዙ ፊልሞችን በምርጥ ሁኔታ ተውናለች። የልቧ መሻት ሆኖ የሙዚቃ አለምን ተቀላቅላ ተወዳጅ ሆናለች። አሁን በቅርቡ ደግሞ በሀገሪቱ ላይ መነጋገሪያ በሆነው አዜብ_ወርቁ ባዘጋጀችው አስደማሚ ፊልም መሰል ድራማ (እረኛዬ) ላይ በመሪ ተዋናይነት እየሰራች አስደማሚ ብቃቷን እያሳየች ነው።

የስብዕና ጥግ፣ የመልካም ሴት አምባሳደር፣ አንደበተ ርቱዕ ጀግኒት ሴት #ሳያት_ደምሴ ናት🙌

Nebil #selamshowbiz

1 year ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.