Logo
YenetaTube
የዘንድሮው ሰላም ኖቤል ሽልማት ለደቡብ አፍሪቃዊቷ ዳና ናቫኔተም ተሰጠ

ደቡብ አፍሪቃዊቷ ዳና ናቫኔተም በአጭሩ ስማቸዉ "ናቪ" ፒላይ የዘንድሮዉን የጎርጎሮሳዉያኑን የ 2026 የኖቤል የሰላም ሽልማት አሸናፊ የሆኑት ፤ለሰላም እና ለዓለም አቀፍ ህግ መከበር ላደረጉት ጥረት መሆኑን የኖቬል ሽልማት ኮሚቴዉ ዛሬ ኖርዌ መዲና ኦስሎ ላይ ይፋ አድርጓል።
እንደ ኖቤል ኮሚቴው ገለጻ፣ በዚህ ዓመት ለሰላም ሽልማቱ በአጠቃላይ 287 እጩዎች ቀርበዉ ነበር። ከእጩዎቹ መካከል፤ በተለይ የዩክሬን የሰብአዊ እና የህፃናት መብት ተሟጋች ማይኮላ ኩሌባ፣ የህፃናት እርዳታ ድርጅት "ሴቭ ዘ ችልድረን" እና መንግስታዊ ያልሆነው የጋዜጠኞች ጥበቃ ኮሚቴ ፤ ያሸንፉሉ ተብለዉ ከተጠበቁት መካከል ነበሩ።
ሽልማቱ በዓለም ዙሪያ የጦር መሳሪያ ለማስፈታት እና ለሰላም በሚደረግ ጥረት ላይ ለሚተጉ ሰዎች እና ቡድኖች የሚበረከት ነዉ።

የኖርዌ የሰላም ሽልማት ከጎርጎረሳዉያኑ 1901 እስከ 2025 ባለው ጊዜ ለ143 ተሸላሚዎች በድምሩ 106 ጊዜ በዘርፉ ሽልማት ተሰጥቷል።
በጎርጎሪያኑ 2019 ዓ.ም የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ.ር አብይ አህመድ የሰላም ኖቤል ሽልማት አሸናፊ መሆናቸው ይታወሳል።

DW Amharic

2 days ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.