(ዘ-ሐበሻ ዜና) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ዛሬ ባሳለፉት አዲስ የሹመት ውሳኔ፣ አቶ ፍሰሃ ደሳለኝን በሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ አስተባባሪ አድርገው ሾመዋል። ይህ ሹመት መንግስት በከፍተኛ የአመራር እርከን ላይ እያደረገ ያለው ሰፋ ያለ ሽግሽግ አካል ነው።
እንደሚታወሰው ዘ-ሐበሻ ከሳምንት በፊት የውስጥ ምንጮቹን ዋቢ በማድረግ፣ አቶ ፍሰሃ ደሳለኝ በቅርቡ ወደ ከፍተኛ የመንግስት ሹመት እንደሚመጡ ቀድሞ ለተከታታዮቹ አድርሶ ነበር። ተሿሚው ከዚህ ቀደም በመቄት ምርጫ ክልል 1 ለክልል ምክር ቤት በብልጽግና ፓርቲ ዕጩ ሆነው ቀርበው እንደነበር መረጃዎች ያሳያሉ። በብልጽግና ፓርቲ የአማራ ክልል ቅርንጫፍ ጽሕፈት የአደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊም::
አዲሱ በሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ አስተባባሪነት የሥራ መደብ፣ የሀገሪቱን የፖለቲካ ምህዳር የማስፋት፣ የተቋማትን አሰራር የማሻሻል እና የዴሞክራሲ ግንባታ ሒደቶችን በበላይነት የማስተባበር ቁልፍ ኃላፊነት የሚወስድ ይሆናል። አቶ ፍሰሃ በዚህ የኃላፊነት ቦታ ላይ መንግስት የጀመራቸውን የፖለቲካ ሪፎርሞች በቅርበት እንደሚከታተሉ ይጠበቃል።
____
ወቅታዊ እና የተረጋገጡ መረጃዎችን ቀድመው ለማግኘት የዘ-ሐበሻ ገጽን ፎሎው ማድረጋችሁን አትርሱ!

2 days ago