ኤርትራ፤ የኢትዮጵያን የወረራ ክስ አስተባበለች!!
የኤርትራ ማስታወቂያ ሚንስትር የማነ ገብረአብ «እጅግ ከፍተኛ ድፍረት እና አታላይነት! » በሚል ርዕስ ዛሬ በኤክስ ገፃቸው ባወጡት መግለጫ፤ ኢትዮጵያ በኤርትራ ላይ ሉአላዊነትን በሚፃረር መልኩ ትንኮሳ ስትፈፅም ቆይታለች ብለዋል።
የማነ «ሊካዱ የማይችሉ እውነታዎች» በሚል አስረጅ ያሏቸውን ስድስት ነጥቦች ጠቅሰው ዛሬ ባወጡት መግለጫ፤ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ በጎርጎሪያኑ ጥቅምት 13 ቀን 2023 ዓ.ም ለፓርላማው ባደረጉት ንግግር፣ መንግስታቸው "የሚቻል ከሆነ በድርድር ካልሆነም በኃይል የባህር በር እንደሚያገኝ» መግለፃቸውን ጠቅሰዋል።
ይህም «ኢትዮጵያ በተግባር በኤርትራ ላይ የጥቃት ጦርነት ማወጇ ነው» ሲሉ የኤርትራው ማስታወቂያ ሚንስትር ገልፀዋል።
ያም ሆኖ ኤርትራ በእነዚህ «ግራ አጋቢ» ላሏቸው የኢትዮጵያ መግለጫዎችና ክስተቶች በ«አርአያነት በሚጠቀስ» ባሉት «መረጋጋትና ትዕግስት ምላሽ ሰጥታለች» ብለዋል።
ለጦርነት ዕቅዱ ከአገር ውስጥ ደጋፊዎቹ ድጋፍ ለማሰባሰብ የኢትዮጵያ መንግስት ተከታታይ ቅስቀሳ አድርጓል ብለዋል።
በተጨማሪም፣ ከኤርትራ ነጻነት ጋር በተያያዘ «በኢትዮጵያ መንግሥት ማህደሮች ውስጥ ማለትም በካቢኔ፣ በፓርላማ እና በሌሎችም ምንም ዓይነት ህጋዊ ሰነድ ማግኘት አልተቻለም» በሚል የኤርትራን ነጻነት ለማጣጣልና ለመካድ ተሞክሯል ሲሉ አቶ የማነ የኢትዮጵያን መንግስት ኮንነዋል።
Seledadotio

22 hours ago