Logo
TIKVAH-SPORT
ሜኬል አርቴታ በወይራ ዛፍ ምን አስተማሩ ?

ስፔናዊው የአርሰናል ዋና አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ በትውልድ መንደራቸው ስፔን ውስጥ የወይራ ዛፎች አሏቸው።

ሚኬል አርቴታ አርሰናልን ሲረከቡ ክለቡ በጥሩ መንገድ ላይ እየተጓዘ ባለመሆኑ የተለያዩ ነገሮችን አስበው እንደነበር ተገልጿል።

አርቴታ በወቅቱ ቃል ከመግባት ይልቅ በጠንካራ ስራ ትልቅ ነገር መገንባት እንደሚቻል ማሳየት ፈልገው ነበር።

ለዚህም እቅዳቸው አርቴታ ከአርሰናል እኩል 140 አመት እድሜ ያለው የወይራ ዛፋቸውን ከስፔን አምጥተው ቢሯቸው ፊት መትከላቸው ተነግሯል።

የአርሰናል አትክልተኛ ረጅም እድሜ ያለው ዛፍ ቦታ መቀየር ሊያጠፋው ይችላል የሚል ስጋቱን ገልፆላቸው ነበር።

ይሁን እንጂ ሚኬል አርቴታ በራሳቸው ዛፉን ዕለት ተዕለት መንከባከባቸው ተገልጿል።

ሚኬል አርቴታ የወይራ ዛፉን ስኬት በትዕግሥት እና ለጥቃቅን ነገሮች ትኩረት በመስጠት እንደሚመጣ ማስተማሪያነት መጠቀማቸው ተነግሯል።

@tikvahethsport      kidusyoftahe
2 days ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.