የዱር አራዊት ውሃ ይጠማቸዋል ብሎ በማሰብ በቦቲ መኪና ያሉበት ፓርክ በመሄድ ውሃ የሚገለብጥላቸው ሰው
በኬንያው የጸቮ ብሔራዊ ፓርክ በበጋው ወቅት የሚከሰተው ከባድ ድርቅ የብዙ አራዊትን ሕይወት አደጋ ላይ ይጥል ነበር። ይሁን እንጂ ፓትሪክ ኪሎንዞ ሙዋልዋ የተባለ በጎ አድራጊ የጽኑ ፍቅርና ርኅራኄ ማሳያ የሚሆን ታሪክ አስመዝግቦ አልፏል።
“የጸቮ ውኃ አቀባይ” በመባል የሚታወቀው ፓትሪክ፡ ለዓመታት የሙቀት መጠኑ በጨመረ ቁጥር በየቀኑ በውኃ ቦቲዎች ብዙ ሺህ ሊትር በመያዝ በፓርኩ ውስጥ ጊዜያዊ ሐይቆችን ይሞላ ነበር።
ዝሆኖች፣ ጎሾች እና የዱር አህዮች የሞተሩን ድምፅ ሲሰሙ በደስታ ወደ ውኃው ይጎርፉ ነበር።
ከአምስት አመት በፊት በሕመም ምክንያት ከዚህ ዓለም በሞት ቢለይም፡ የጀመረው በጎ ሥራ በፈጠረው ድርጅት አማካኝነት ዛሬም ድረስ የበርካታ አራዊትን ሕይወት ከመታደግ አልፎ ዓለም አቀፍ አርአያነቱን አስመስክሯል።
Seledadotio

2 days ago