Logo
Zehabesha
(ዘ-ሐበሻ ዜና) ‹‹ሩሲያ የዶምባስን ህዝብ ለማውደም እየሞከረች ነው›› ሲሉ ዘለንስኪ ተናገሩ፡፡ በዛሬው እለት በዶምባስ ግዛት በሚገኘው ክራማቶርስክ ከተማ በተፈፀመ ጥቃት ሁለት የህዝብ ማመላለሻ አውቶቡሶች መመታታቸውን የአካባቢው ባለስልጣናት ገለፁ፡፡ የዩክሬይኑ ፕሬዝደንት ቮሎዶሚር ዘለንስኪ ጥቃቱን አስመልክተው በኤክስ ገፃቸው ላይ በፃፉት አስተያየት ‹‹በጥቃቱ እስካሁን ባለኝ መረጃ 30 ሰዎች መገደላቸውን አረጋግጫለሁ፡፡ ህይወት ለማዳን የሚደረገው ጥረት እንደቀጠለ ቢሆንም በሚያሳዝን ሁኔታ የሟቾች ቁጥር ሊጨምር ይችላል፡፡

ከደረሰው ጥቃት የተነሳ የአንዳንዶቹ ተጎጂዎች ማንነት ሊለይ አልቻለም›› ካሉ በኋላ 18 ሰዎች መቁሰላቸውን አስታውቀዋል፡፡ ከአውቶቡሶቹ በተጨማሪ በከተማው ውስጥ በመኖሪያ ህንፃዎችና መኪናዎች ላይም ጉዳት መድረሱን የጠቀሱት ዘለንስኪ ለዚህ ጥቃት መልስ እንደሚሰጡም ገልፀዋል፡፡ ጨምረውም ‹‹ሩሲያ የዶንባስን ህዝብ ለማውደም እየሞከረች ነው፡፡ ስለዚህም ከአለም አቀፉ ማህበረሰብ ግብረ መልስ ያስፈልጋል፡፡ ሩሲያዊያን ላጠፉት የሰው ህይወት ተመጣጣኝ የሆነ ጠንካራ ምላሽ ሊሰጣቸው ይገባል›› በማለት ጥሪ አቅርበዋል፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ ዘለንስኪ ይህንን ከፃፉ በኋላ የሟቾች ቁጥር 33 መድረሱ ተዘግቧል፡፡

2 days ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.