Logo
TIKVAH-SPORT
“ የመጨረሻ ውሳኔው ዛሬ አይነገርም ” TAS

ባለፈው የአፍሪካ ዋንጫ አሸናፊነት ውዝግብ ዙሪያ ሴኔጋል ፣ ሞሮኮ እና ካፍ በክስ ላይ መሆናቸው ይታወቃል።

ጉዳዩ ወደ አለም አቀፉ የስፖርት ገላጋይ ፍርድ ቤት ማምራቱ የሚታወቅ ሲሆን ካስ ጉዳዩን ዛሬ ለማየት ቀጠሮ ይዞ ነበር።

የካስ ዋና ዳይሬክተር ማቲው ሬብ ከችሎቱ በፊት በሰጡት ቃል “ ውሳኔው ዛሬ ወይም ነገ አይታወቅም " ብለዋል።

“ ነገርግን በሚቀጥሉት ቀናት እናውቃለን “ ሲሉ ካስ በተቻለ ፍጥነት ፍርድ መስጠት እንደሚፈልግ አረጋግጠዋል።

የፍርድ ሂደቱ ለህዝብ ክፍት እንዲሆን የጠየቀ አካል ባለመኖሩ በዝግ እንደሚደረግ ተገልጿል።

@tikvahethsport      kidusyoftahe የሴኔጋል እና ሞሮኮ ክርክር ከምን ደረሰ ? ባለፈው የአፍሪካ ዋንጫ አሸናፊነት ውዝግብ ዙሪያ ሴኔጋል ፣ ሞሮኮ እና ካፍ በክስ ላይ መሆናቸው ይታወቃል። ሴኔጋል ጨዋታውን አሸንፋ የነበረ ቢሆንም ካፍ ከሜዳ ወጥተዋል በሚል አሸናፊነቱን ለሞሮኮ መስጠቱ አይዘነጋም። በዚህም ምክንያት የሴኔጋል እግርኳስ ፌዴሬሽን ጉዳዩን ወደ አለም አቀፉ የስፖርት ገላጋይ ፍርድ ቤት " TAS " ወስዶታል። አሁን ላይ…
2 days ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.