የዓለም ሻምፒዮኑ ጀግናው ክብሮም ንጉሴKebrom muaythia and kickboxing champion . ደማቅ የእውቅና እና የምስጋና ፕሮግራም ሊደረግለት ነው!
የሀገራችንን ሰንደቅ ዓላማ በዓለም አቀፍ መድረክ ላይ ከፍ ላደረጉ፣ የኢትዮጵያን ስም በኩራት ላስጠሩ ጀግኖች እውቅና መስጠትና ማበረታታት የሁላችንም ታሪካዊ ድርሻ ነው!
ኢትዮጵያውስጥ Ethio Fight Night አሸናፊ እንዲሁም
በታኅሣሥ ወር 2023 ዓ.ም (December 2023) በጣሊያን ሀገር በታዋቂው Fight Clubbing አዘጋጅነት በተካሄደው የዓለም የሞይታይ ሻምፒዮና (Muay Thai World Championship) ላይ በ67 ኪሎ ግራም ክብደት ሙሉ ኢትዮጵያን ወክሎ በመወዳደር፣ የዓለም ሻምፒዮን (World Champion) በመሆን የወርቅ ሜዳሊያ ያስገኘውና የሀገር ኩራት የሆነው የሳሪስ አዲሱ ሰፈር ልጅ ክብሮም ንጉሴ (The King) ታላቅ የክብር እና የምስጋና መርሃ ግብር ተዘጋጅቶለታል።
ክብሮም ንጉሴ በዓለም አቀፍ የማርሻል አርት መድረኮች (እንደ Bellator እና WPG Combat ያሉ) የብራዚልና የሌሎች ሀገራት ጠንካራ ተፎካካሪዎችን በበላይነት በመርታት የሚታወቅ፣ የሁለት ጊዜ የጣሊያን K1 ሻምፒዮን እና የኢንተርኮንቲኔንታል ሻምፒዮን በመሆን በፅናትና በደምና በላቡ የተጓዘ እውነተኛ የኢትዮጵያ አልማዝ ነው።
ይህንን ታላቅ ድል እና የሀገር ባለውለታ በደማቅ ሁኔታ ለመዘከር፣ መላው የሳሪስ ወጣቶች ከተለያዩ አጋር ድርጅቶችና ባለድርሻ አካላት ጋር በመተባበር ደማቅ የምስጋና እና የእውቅና መርሃ ግብር (Appreciation & Recognition Ceremony) አዘጋጅተዋል።
ይህ የምስጋና እና የእውቅና መርሃ ግብር ከ 500 በላይ ታዳሚዎች የሚሳተፉበት ሲሆን፣ የኢትዮፋይት (EthioFight)night )&etfc አዘጋጆች ፡ተወዳዳሪዎች እና አዘጋጆች፣ ታዋቂ የማህበራዊ ሚዲያ ተፅዕኖ ፈጣሪዎች፣ የሳሪስ ወጣቶችና የአካባቢው ማህበረሰብ እንዲሁም የክብር እንግዶችና አጋር ድርጅቶች በነቂስ የሚገኙበት ይሆናል።
የሰፈራችንን፣ የከተማችንንና የሀገራችንን ጀግና በጋራ ሆነን እንቀበለው፤ እናበረታታው! ሁላችሁም ሚዲያዎችና ስፖርት አፍቃሪዎች በዚህ ታሪካዊ ፕሮግራም ላይ እንድትታደሙ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን።

3 days ago