(ዘ-ሐብሻ ዜና) የኢትዮጵያ መንግስት በአዲስ አበባ የሚገኙትን አንድ የግብጽ ዲፕሎማት ማባረሩን ተከትሎ፣ ካይሮ በአጸፋው በግብጽ የኢትዮጵያ ኤምባሲ አማካሪ የሆኑትን ዲፕሎማት ሀገር ለቀው እንዲወጡ አዘዘች። ዲፕሎማቱ በ48 ሰዓታት ውስጥ ግብጽን ለቀው እንዲወጡ ተነግሯቸዋል።
ይህ የካይሮ እርምጃ የመጣው ኢትዮጵያ ትላንት ሐሙስ ዕለት አህመድ ሞሀረም አህመድ ሱሊማን የተባሉትን የግብጽ ኤምባሲ ሰራተኛ "ፐርሶና ነን ግራታ" ማወጅ በ48 ሰዓታት ውስጥ ከሀገር እንዲወጡ ማዘዟን ተከትሎ ነው።
የግብጽ መንግስት ምንጮች የኢትዮጵያን ውሳኔ "የሚያሳዝን" እና ተገቢነት የሌለው ሲሉ ተችተውታል። አንድ ስማቸው ያልተጠቀሰ የግብጽ ባለስልጣን እንደገለጹት፤ "ካይሮ በዓለም አቀፍ ህግ እና በተባበሩት መንግስታት ድርጅት (UN) ቻርተር መሰረት፣ በሌሎች ሉዓላዊ ሀገራት የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ መግባትን አጥብቃ ትቃወማለች" ብለዋል።
በተጨማሪም ምንጩ የኢትዮጵያን መንግስት በከፍተኛ ሁኔታ የወነጀሉ ሲሆን "የኢትዮጵያ መንግስት ለሚያጋጥሙት የውስጥ ፈተናዎች እና ሀገራዊ ቀውሶች የውጭ ኃይሎች ጣልቃ ገብተዋል እያለ ማመካኘት ልማድ አድርጎታል" ሲሉ ከሰዋል።
ግብጽ ይህንን የዲፕሎማት ማባረር እርምጃ የወሰደችው ዓለም አቀፉን "የአጸፋ መርህ" (Principle of reciprocity) መሰረት በማድረግ መሆኑን በማረጋገጥ፣ የኢትዮጵያው ዲፕሎማት በተመሳሳይ በ48 ሰዓታት ውስጥ ሀገር ለቀው መውጣት እንዳለባቸው አስታውቃለች።
_____
🗣 የዘ-ሐበሻ አጭር ማስታወሻ፡ ከኤርትራ ጋር ሙሉ ለሙሉ የተቋረጠው ግንኙነት እና አሁን ደግሞ ከግብጽ ጋር የተገባው የዲፕሎማቶች መባረር ፉክክር፤ የአፍሪካ ቀንድን የፖለቲካ ውጥረት ወደ አዲስ እና አደገኛ ምዕራፍ አሸጋግሮታል። ይህ የካይሮ እና የአዲስ አበባ እሰጣ ገባ በቀጠናው ላይ ምን ዓይነት የጸጥታ መዘዝ ይዞ ይመጣል ብላችሁ ታስባላችሁ?

9 days ago