በስህተት ጤናማ እግሯ የተቆረጠባት አሜሪካዊት ሁለቱንም እግሮቿን አጣች
በአሜሪካ ኦሃዮ ግዛት የምትገኝ ሻሮን ጃክስ የተባለች የካንሰር ታካሚ በሴልቢ ጄኔራል ሆስፒታል ለቀዶ ጥገና በገባችበት ወቅት በህክምና ቡድኑ በፈጸመው ከባድ ስህተት ህይወቷ ተለውጧል።
WBNS እንደዘገበው ታካሚዋ የታመመው የቀኝ እግሯ እንዲቆረጥ ወደ ሆስፒታል ብትገባም፡ ሀኪሞቹ በስህተት ጤናማውን የግራ እግሯን ቆርጠውታል።
ከቀዶ ጥገና በኋላ ከእንቅልፏ ስትነቃ ያልታመመው እግሯ መቆረጡን ያወቀችው ሻሮን፡ በኋላ ላይ የቀኝ እግሯም መቆረጥሁለቱንም እግሮቿን ለማጣት ተገዳለች።
የታካሚዋ ጠበቃ እንደገለፁት፡ ከቀዶ ጥገናው በፊት የቀኝ እግሯ በግልጽ የተቀመጠ መለያ ምልክት የነበረው ቢሆንም የህክምና ቡድኑ ግን ስህተቱን ፈፅሟል።
ሆስፒታሉ የሰራተኞቹን ጥፋት ያመነ ሲሆን፡ ከጉዳዩ ጋር እጃቸው ያለበት ሰራተኞች ከስራ መባረራቸውን አስታውቋል።
አሁን ላይ ተጎጂዋ በሆስፒታሉ እና በህክምና ቡድኑ ላይ የካሳ ክስ መስርታለች።
Seledadotio

10 days ago