(ዘ-ሐበሻ ዜና) የፍላይ ዱባይ አየር መንገድ ንብረት የሆነው አውሮፕላን ዛሬ ከዱባይ ተነስቶ ወደቴሌአቪቭ እየበረረ ነበር፡፡ በአውሮፕላኑ ውስጥ 27 ህፃናትን ጨምሮ 174 ተሳፋሪዎች ነበሩበት፡፡ አውሮፕላኑ በበረራ ላይ እያለ የበረራ መቆጣጠሪያ ክፍል(ኮክፒት) ውስጥ አንድ ድርጊት ይፈፀማል፡፡ እንደዘገባዎች ከሆነ የኦማን ዜግነት ያለው ረዳት ፓይለቱ አውሮፕላኑን ለመከስከስ ጥረት በሚያደርግበት ወቅት ከዋናው ፓይለት ጋር ፀብ ውስጥ ይገባል፡፡
ይህ ፀብ ወደድብድብ ካመራ በኋላ ከመቆጣጠሪያ ክፍሉ ውጭ ያሉት መንገደኞች ሁኔታውን ለመረዳት ችለዋል፡፡ ይህንን ተከትሎም ተሳፋሪዎቹ ከመቀመጫው በመነሳት የኤመሬትስ ዜግነት ያለውን ዋናውን ፓይለት በማገዝ በረዳቱ ላይ ከፍተኛ ጉዳት ማድረሳቸው ተዘግቧል፡፡ የእስራኤል ባለስልጣናት ድርጊቱ የረዳት ፓይለቱ ራስን በራስ የማጥፋት ሙከራ ሊሆን እንደሚችል ገልፀው በጉዳዩ ላይ ምርመራ ማድረግ መጀመራቸውን አስታውቀዋል፡፡
በወቅቱ የነበረው ፀብ ቀላል እንዳልነበር አንዳንድ ተሳፋሪዎች የለበሱት ቲሸርት ደም እንደነካው በሚያሳ ፎቶ ገልፀዋል፡፡ ፍላይት ራዳር 24 እንደገለፀው በዚህ ድብድብ ወቅት አውሮፕላኑ ያልተለመደ ከፍና ዝቅ የማለት ሁኔታ ታይቶበት ነበር፡፡ አንድ ቦታ ላይ ከ34,000 ጫማ ከፍታ በፍጥነት ወደ 14,000 ጫማ ወርዶ እንደነበርም አስረድቷል፡፡ ከዚህ ሁሉ ውጥረት በኋላ አውሮፕላኑ ለሳኡዲ አረቢያ ሲቪል አቪየሽን ድንገተኛ መልእክት ካስተላለፈ በኋላ በሰላም ለማረፍ ችሏል፡፡

9 days ago