Logo
YenetaTube
አቶ ሳሙኤል ሞላልኝ የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ እና የፕላን ልማት ቢሮ ኃላፊ ሆነው ተሾሙ

የአዲስ አበባ ምክር ቤት አቶ ሳሙኤል ሞላልኝን የከተማዋ ምክትል ከንቲባ እና የፕላን ልማት ቢሮ ኃላፊ አድርጎ ሾሟል፡፡ ቀደም ሲል የደሴ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ የነበሩ ሲሆን በተለያዩ የስራ ሃላፊነቶች አገልግለዋል፡፡

በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የተለያዩ ሹመቶችን ለከተማ አስተዳደሩ ምክር ቤት አቅርበዋል። በዚሁ መሠረት፤

👉 አቶ ሚሊዮን ማቲዎስ በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ሥራ እና ክህሎት ኃላፊ

👉 አቶ ጥላሁን ከበደ በምክትል ከንቲባ ማዕረግ በአዲስ አበባ ከተማ የፐብሊክ ሰርቪስ እና የሰው ሃብት ልማት ቢሮ ኃላፊ

👉 አቶ ሀፍታይ ገብረእግዚአብሄር በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የባህል እና ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ

👉 አቶ አብዱልቃድር ሬድዋን በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ የፋይናንስ ቢሮ ኃላፊ በመሆን በከንቲባዋ የቀረቡ ናቸው።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የቀረቡትን ሹመቶች አጽድቋል።

Ethiopian press Agency

11 days ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.