Logo
TIKVAH-MAGAZINE
ቡርኪና ፋሶ የመጀመሪያውን የወርቅ ማጣሪያ ፋብሪካ ሥራ አስጀመረች።

የቡርኪና ፋሶ የሽግግር መንግሥት ፕሬዚዳንት ኢብራሂም ትራኦሬ የመጀመሪያውን የሀገር ውስጥ የወርቅ ማጣሪያ ፋብሪካ በዋና ከተማዋ ኡጋዱጉ፥ ኦጋ 2000 በተባለው ስፍራ መርቀው በይፋ ሥራ አስጀምረዋዋል።

በመንግስትኛ የግል ባለሃብቶች ጥምረት የተሰራው ይኸው ፋብሪካ ፋብሪካ ግንባታ ወደ 19 ሚሊዮን ዶላር ገደማ ወጪ ተደርጎበታል ሲባል በመጀመሪያው ምዕራፍ በዓመት እስከ 164 ቶን ወርቅ የማጣራት አቅም አለው።

ፋብሪካው ከግዙፍ ኢንደስትሪዎችና ከአነስተኛ ወርቅ አውጪዎች የሚሰበሰበውን ወርቅ በማጣራት የዓለም አቀፍ መስፈርትን የሚያሟላ ምርት የማምረት አቅም አለው ተብሏል።

የቡርኪና ፋሶ ወታደራዊ መሪ ኢብራሂም ትራኦሬ “ምኞታችን ከወርቅ ባሻገር ነው. . . የማዕድን ዘርፉን የሀገሪቱ የኢንዱስትሪ ትራንስፎርሜሽን አነቃቂ ሞተር ማድረግ እንፈልጋለን” ሲሉ ተናግረዋል።

በ2025 ዓ.ም ከ94 ቶን በላይ ወርቅ ያመረተችው ቡርኪና ፋሶ፣ ከአፍሪካ ከፍተኛ ወርቅ አምራች አገራት አንዷ ስትሆን፣ መሰል የወርቅ ማጣሪያ ፋብሪካዎችን በሀገር ውስጥ የመገንባት እንቅስቃሴ በጋና፣ ጊኒ፣ ማሊ እና ኮትዲቯርም እየተስፋፋ ይገኛል።

መስከረም 19 ቀን 2019 ዓ.ም

@TikvahethMagazine
11 days ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.