Logo
4-3-3 ስፖርት በኢትዮጵያ™
የዋልያዉ አለቃ ዮሀንስ ሳህሌ በዛሬዉ ጨዋታ አንድም ጊዜ ሳይቆሙ ሙሉ ጨዋታዉ ተቀምጠዉ መከታተላቸዉ በብዙዎች ዘንድ እያነጋገር ይገኛል።

ከጨዋታዉ መጠናቀቀ በኋላ በነበረዉ ጋዜጣዊ መግለጫ ስለጉዳዩ የተጠየቁት አሰልጣኙ ተከታዩን አስተያየብ ሰጥተዋል።

🗣 "በጨዋታዉ ወቅት ቆሞ ተጫዋቾቹን ሲመራ የነበረዉ ምክትል አሰልጣኜ ነበር። እኔ ሜዳ ላይ ልምምድ አሰራለዉ እሱ ደግሞ ጨዋታ ላይ ይመራል።

ልምምድ ላይ እኛ ስራችንን እንሰራለን ፤ በዛ መሰረት ሜዳ ላይ ደግሞ ተጫዋቾች የሚሰሩትን ጠንቅቀዉ ያዉቃሉ።

አስፈላጊ ታክቲካዊ ነገሮች ሲኖር ቆሜ ላስተላልፍ እችላለዉ ፤ ነገር ግን እኔ ሆንኩ ምክትሌ መቆማችን ለዉጥ የለዉም።"

@Bisrat_sport_433et
@Bisrat_sport_433et
12 days ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.