Logo
SeledaPost
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በሕገወጥ መንገድ ወደ መሬት ባንክ ተዘዋውረዋል የተባሉ የይዞታ ቅሬታዎችን ለመመርመር ኮሚቴ አቋቋመ
 
የከተማው የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ ከ250 በላይ የሚሆኑ የይዞታ ባለቤቶች ያቀረቧቸውን ቅሬታዎች መርምሮ ውሳኔ የሚሰጥ አሠራር መዘርጋቱን አስታውቋል። ቢሮው እንዳለው ቅሬታዎቹ የተነሱት በ2015 ዓ.ም በመላው ከተማ በተካሄደው ባዶ መሬት ጥናትና ኦዲት ሲሆን፣ በወቅቱ 3 ሺህ 744 ሄክታር መሬት (10 ሺህ 97 ይዞታዎች) ከሕገ-ወጥ ይዞታዎች ተመልሰው ወደ መሬት ባንክ እንዲገቡ መደረጉ ተገልጿል።

የመሬት ባንክና ጥበቃ ቡድን መሪ አቶ ክፍሎም አሰፋ እንደገለጹት፤ ኦዲቱ በዘመቻ መልክ የተካሄደ በመሆኑ ቅሬታዎች ሊነሱ ችለዋል። ለዚህም በእያንዳንዱ ክፍለ ከተማ የተቋቋሙት ኮሚቴዎች የእያንዳንዱን ይዞታ ነባራዊ ሁኔታ መርምረው የመጨረሻ ውሳኔ እንደሚሰጡ መግለጻቸውን ብር ሜትሪክስ ዘግቧል።
 
ቢሮው የሕጋዊ ባለቤቶች መብት እንዲከበር እና የመልካም አስተዳደር ችግሮች እንዲቀረፉ፣ እንዲሁም የሕዝብና የመንግሥት መሬት ከወረራ እንዲጠበቅ የተጀመረው የማስተካከያ ሥራ በተቀመጠለት የጊዜ ገደብ መጠናቀቅ እንዳለበት ማሳሰቡም በዘገባው ተመልክቷል።

Seledadotio
Seledadotio
12 days ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.