ከ21 ዞኖች ወደ ስድስት‼️
የኦሮሚያ ክልል ስድስት ዞኖች ብቻ እንዲኖሩት የሚያደርግ አዲስ አደረጃጀት የተካተተበት አዋጅ በጨፌ ኦሮሚያ ጸደቀ።
በኦሮሚያ ክልል ምክር ቤት መስራች ጉባኤ ላይ ዛሬ ሰኞ መስከረም 18፤ 2019 የጸደቀው አዋጅ፤ ለዞኖች “ለመጀመሪያ ጊዜ የህግ ማዕቀፍ እና የመወሰን ስልጣን የሰጠ ነው” ተብሏል።
ዛሬ ከሰዓት በተካሄደው የጉባኤው ውሎ በሙሉ ድምጽ የጸደቀው ይህ አዋጅ፤ “የኦሮሚያ ክልል ዞኖች፣ ወረዳዎች እና ቀበሌዎች፤ የአስፈጻሚ አካላትን አደረጃጀት፣ ስልጣንና ተግባር ለመወሰን” የወጣ እንደሆነ ተገልጿል።
እስከ ዛሬ በስራ ላይ የቆየው የክልሉ አደረጃጀት፤ የኦሮሚያ ክልልን በ21 ዞኖች ያዋቀረ ነበር።
አዲሱ አደረጃጀት ግን የኦሮሚያ ክልልን በአቅጣጫ ላይ በተመሰረቱ ዞኖች መልሶ የሚያዋቅር ይሆናል።
በዚህ መሰረት አዳዲሶቹ ስድስት ዞኖች፤ “ምስራቅ”፣ “ምዕራብ”፣ “ማዕከላዊ”፣ “ደቡብ”፣ “ደቡብ ምዕራብ” እና “ደቡብ ምስራቅ” የሚል ስያሜ ተሰጥቷቸዋል።
Seledadotio

12 days ago