"አላማችን አንድ እውቅ ሰው መፍጠር ነው"
#ethiopia I ለሚቀጥሉት አምስት አመታት አብረው ለመስራት ስምምነት ያደረጉት ቪዠነሪ ሶሉሽን እና ጆርዳን ቢውቲ አካዳሚ በስነ ውበቱ ዘርፍ ብቁና ታዋቂ የሆነ ስም ለመፍጠር ነው ስምምነት ያደረግነው ብለዋል።
ይህ የአጋርነት ስምምነት በኢትዮጵያ የውበት ኢንዱስትሪ ውስጥ ትልቅ የዕድልና በር የሚከፍትም ነው ተብሎለታል።
ፓን ኣፍሪካን ኤጁኬሽን ኤንድ ስኪልስ ንዑስ ድርጅት ወይም ሰብ ሲደሪ የሆነው Visionary Solutions እና Jordan Beauty Academy አጋርነታቸውን የሚያረጋግጥ ስምምነት አድርገዋል።
ስምምነትም ለቀጣዩ አምስት አመታት በመፅናት Jordan Beauty Academy አለም አቀፋዊ እውቅናን ተግቶ ለሚሰራው ባለሙያ የሚሰጥ ብቸኛ ኢትዮጵያዊ ተቋም ያደርገዋል ነው የተባለው።
በኢትዮጵያ ውስጥ እንደ Prometric እና CIDESCO ያሉ አለም አቀፋዊ ደረጃቸዎች ላይ የተመሰረቱ የውበት ስልጠና እና የሙያ ሰርተፊኬሽን ስርዓቶችን ተደራሽ የሚያደርግ ስምምነት በመሆኑ በሃገራችን ብሎም በአህጉራችን ያለውን የፋሽን እና ውበት ጥራት ከፍ የሚያድርግ ስምምነት እንደሆነም ነው የተገለፀው።
በዚህ ስምምነት ምክንያት ተደራሽነቱ ከፍ የሚለው የብቃት ማረጋገጫ ዕውቅና የሀገራችን ባለሙያዎች ለመጀመርያ ጊዜ በዩናይትድ አረብ ኤምሬትስ፣ በአውሮፓ እና በአሜሪካ የሚገኘው የስራ ገበያ ላይ ተወዳዳሪ እንዲሆኑ ያስችላቸዋል ቸብሏል።
ይህ ጥምረት በኢትዮጵያ ቀዳሚ በመሆን አለም አቀፍ የፈተና እና የምስክር ወረቀት ሰጪ እንዲሁም በከፊል የሰለጠኑና የሰለጠኑ ባለሞያዎችን (semi skilled and skilled workforce) ወደተለያዩ የዉጭ ሃገራት ስምሪትን የሚያሳልጥ ስምምነት ነው።
ፓን ኣፍሪካን ኤዱኬሽን ኤንድ ስኪልስ ንዑስ አካል ወይም ሰብ ሲደሪ የሆነውን Visionary Solutions የረዥም አመት የውበት ኢንዱስትሪ ቆይታ ካለው እና ከ2ሺህ 500 በላይ ባለሙያዎችን ካፈራው Jordan Beauty Academy ጋር በማገናኘት በዘርፉ ያለውን ባለሙያ ተውዳዳሪነት ይጨምራል ብለዋል።
ከዚህ ቀደም በሀገር አቀፍ ደረጃ እውቅና ያላቸው ባለሙያዎች የCIDESCO መስፈቶችን የሚያሟላ አጭር ስልጠና የሚያገኙበትን አጋጣሚ ይፈጠርላቸዋል ተብሏል።
ከስልጠናውም በኋላ በዩናይትድ አረብ ኤምሬትስ፣ በአውሮፓ እና በአሜሪካ ለመስራት የሚያስችላቸውን ዕውቅና የራሳቸው ማድረግ ያስችላቸዋል ተብሏል።
በVisionary Solutions እና Prometric በኩል የሚገኘውም ዕውቅና ባለሙያዎች የሚኖራቸውን አለም አቀፍ ተወዳዳሪነት ከፍ ያደርገዋል እንደሚያደርገውም ነው የተገለፀው።

1 year ago