Logo
Zehabesha
(ዘ-ሐበሻ ዜና) በጦርነት እና በመጠፋፋት አዙሪት ውስጥ ለምትገኘው ኢትዮጵያ፣ የሃይማኖት አባቶች የሰላም ጥሪ ከፖለቲከኞች የጦርነት ነጋሪት ጋር ግብግብ ከገጠመ ሰነባብቷል። የሚኒሶታ እና አካባቢው ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ አቡነ ናትናኤል ዛሬ በሚኒሶታ ሴንት ፖል ከተማ፣ የመስቀል ደመራ በዓል ሲከበር ለተሰበሰበው ምዕመን ያደረጉት ልብ የሚነካ የምርቃት እና የጸሎት ቃል፣ የሀገሪቱን ወቅታዊ እና አሳዛኝ የፖለቲካ እውነታ ገልጦ የሚያሳይ ሆኖ ተገኝቷል።

ሊቀ ጳጳሱ በጸሎታቸው "በየጊዜው እና በየስፍራው የምንሰማውን ጦርነቱን፣ ችግሩን፣ መገዳደሉን፣ መጠፋፋቱን ሁሉ እግዚአብሔር አምላክ ያስወግድልን" ሲሉ ተማጽነዋል። ይህ ጸሎት መሬት ላይ ካለው የኢትዮጵያ እውነታ ጋር ሲነጻጸር ግን የልብ ስብራት ይፈጥራል። ዛሬ ላይ ከሰሜን እስከ ደቡብ፣ ከምስራቅ እስከ ምዕራብ፤ በተለይም በአማራ፣ በኦሮሚያ፣ በአፋር እና ዳግም አዲስ የጦርነትና የውጥረት ደመና ባንዣበበባት ትግራይ ክልሎች ውስጥ ዜጎች የዕለት ተዕለት ኑሯቸው ከመገዳደል እና ከስጋት ጋር የተቆራኘ ሆኗል። የፖለቲካ ልሂቃኑ የሥልጣን ቼዝ ሲጫወቱ፣ ገበሬው ማሳውን ትቶ ጥይት እንዲያርሰው ተፈርዶበታል።

በተለይም አቡነ ናትናኤል "ዘመኑ የጠመንጃ አፈሙዝ አፍ የሚዘጋበት ያድርግልን... ጦርነቱን ያስወግድልን" በማለት ያቀረቡት ምኞት በሽ*ብር እና በጠመንጃ ኃይል ብቻ ፖለቲካዊ የበላይነትን ለማረጋገጥ ለሚሽቀዳደሙት የሀገራችን ታጣቂ ኃይሎች እና መንግስታዊ መዋቅሮች ትልቅ የህሊና ጥያቄ የሚያጭር ነው። አፈሙዝ መዝጋት ያልቻለች ሀገር፣ እንዴት የዜጎቿን የዕለት ጉርስ መሙላት ትችላለች? የትግራይ፣ የአማራ፣ ኦሮሚያ እና የአፋር አዋሳኝ አካባቢዎች በጦርነት ጠባሳ ገና ሳያገግሙ ዳግም ወደ እሳት እና ወደ አዲስ መፈናቀል እየተገፉ መሆናቸው የዚሁ ማሳያ ነው።

በጣም ልብ የሚነካው እና የሀገራችንን የሞራል ውድቀት የሚያሳየው ሌላኛው የሊቀ ጳጳሱ ጸሎት ደግሞ "አረጋውያን ሽማግሌዎች በሰላም የሚጦሩባት፣ ልጆቻቸውን የሚመርቁባት ያድርግልን" የሚለው ነው። በተጨባጭ ግን ዛሬ በኢትዮጵያ የተለያዩ አካባቢዎች አረጋውያን ልጆቻቸውን የመመረቅ ዕድል ተነፍገዋል። በየጦር ግንባሩ በከንቱ የሚረግፉትን ልጆቻቸውን በየዕለቱ እየቀበሩና እያለቀሱ ይገኛሉ። የባሰባቸው ደግሞ በስተእርጅና ዘመናቸው ቀያቸውን ጥለው በየመጠለያ ካምፑ ለልመና እና ለእንግልት ተዳርገዋል።

አቡነ ናትናኤል ዜጎች "በሰላም ወጥተው በሰላም የሚገቡባት" ሀገር እንድትኖረን ተመኝተዋል። ይሁን እንጂ ዛሬ ላይ ከአንዱ ክልል ወደ ሌላው ክልል በሰላም ተጉዞ መመለስ የቅንጦት ያህል ርቆናል። መንገዶች በእ*ገታ፣ ግ*ድያ እና በጥቃቶች ታጥረዋል።

የሃይማኖት አባቶች ጸሎት እና የምህረት ልመና የራሱ የሆነ መንፈሳዊ ቦታ ቢኖረውም፣ አፈሙዝ የጨበጡትና የፖለቲካውን መዘውር የሚዘውሩት አካላት ለሰው ልጅ ህይወት ክብር እስካልሰጡ ድረስ፣ ይህች ሀገር ከመጠ*ፋፋት አዙሪት ልትወጣ አትችልም። የሊቀ ጳጳሱ ጸሎት ለፖለቲከኞቻችን የህሊና ደወል ሊሆን ይገባል፤ "ከንቱ ሞት ይብቃ" ተብሎ አፈሙዝ ወደ መሬት የሚዘቅዘቅበት ጊዜ አሁን ነው።

ሰላም ለኢትዮጵያችን!

14 days ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.