Logo
Getu Temesgen
የዶናልድ ትራምፕ ከተማ በጋዛ እና የአውሮፓ ህብረት ልዩ አቋም!
#ethiopia | አሜሪካ ለወትሮም ለእስራኤል የምትሰጠው ድጋፍ አልተቋረጠም፡፡ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ወደ ስልጣን ከመጡ በኋላ ለአፍታም ቢሆን ተኩስ አቁም ተፈጥሮ የነበረ ቢሆንም በተለይ አሜሪካ ጋዛን እንድትቆጣጠር ያመጡት እቅድ ቁጣ ቀስቅሷል፡፡

በየካቲት ወር ፕሬዚዳንቱ 2 ሚሊዮን ፍልስጤማውያንን ከጋዛ አስወጥቶ ወደ ግብጽ እና ጆርዳን በማስፈር ጋዛን በአሜሪካ ባለቤትነት እንደገና መልሶ የማልማት እቅድ ይፋ ማድረጋቸው ይታወሳል፡፡

በእቅዳቸው በጋዛ ሰውሰራሽ ደሴት፣ ወደቦች፣ ፋብሪካዎች እና አለም አቀፍ ቱሪዝምን የሚስብ ልማት ይከናወናል ብለው ነበር፡፡ ይህ የትራምፕ እቅድ ከብዙ አቅጣጫ ተቃውሞ ገጥሞት ነበር፡፡ የአረብ ሃገራት፣ በተለይ እቅዱ የሚነካቸው ግብፅ እና ጆርዳንን ጨምሮ ሌሎችም ህገወጥ ነው ብለው ተችተዋል፡፡

የአውሮፓ ህብረት ሃገራትም የፍልስጤማውያንን በርስታቸው የመኖር መብታቸውን ይነካል ብለው እቅዱን ተችተዋል፡፡ የተመድ ዋና ጸሃፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ እቅዱ የዘር ማጽዳት ወንጀል ነው ብለው ነበር፡፡

እንደ አስገድዶ ህዝብን የማስፈር ያሉ የአለም አቀፍ ህግ የሚከለክላቸውን ወንጀሎች ይጥሳል፣ ፍልስጤማውያንን የማፅዳት ተግባር ስለሆነ ከባድ የሰብዓዊ መብት ጥሰት ነው፣ ቀጠናውን በተለይም ግብጽ እና ጆርዳንን ይረብሻል፣ እንዲሁም የእስራኤል እና ፍልስጤምን ታሪካዊ ችግር ይቀርፋል የተባለውን የሁለት ሃገርነት መፍትሄ ያበላሻል የሚሉት በትራምፕ ዕቅድ ላይ የተነሱ ዋነኞቹ ትችቶች ናቸው፡፡

የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚንስትር ኔታንያሁ የትራምፕን እቅድ ሙሉ ለሙሉ ደግፈው የአፈጻጸም ዝርዝር እቅድ ሁሉ አጋርተው ነበር፡፡
#selamshowbiz

1 year ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.