ማንቸስተር ዩናይትድ የሜዳ ላይ ሳሩን ለሽያጭ ማቅረቡ ግርምትን ፈጠረ
ማንቸስተር ዩናይትድ ቀደም ሲል ባርሴሎና ይጠቀምበት የነበረውን የገቢ ማግኛ መንገድ በመከተል የኦልድ ትራፎርድ ስታዲየሙን የሜዳ ሳር ለደጋፊዎች መሸጥ መጀመሩ ተዘግቧል።
ክለቡ 7 ሴንቲሜትር ስፋት ያለውን የኦልድ ትራፎርድ የሜዳ ሳር በብርጭቆ ዕቃ (Turf Cube) ውስጥ አሽጎ በ125 ፓውንድ ለገበያ አቅርቦታል ተብሏል።
በታዋቂው የስፖርት ዘጋቢ ፖል ሂርስት እና በታዋቂ የስፖርት መገናኛ ብዙኃን ዘገባ መሠረት፣ ማንቸስተር ዩናይትድ የባርሴሎናን የካምፕ ኑ አሰራር በመከተል የታዋቂውን ኦልድ ትራፎርድ ስታዲየም የሜዳ ሳር ለአንደኛ ደረጃ የትኬት ባለቤቶች (Season-ticket holders) እና ለደጋፊዎች መቸርቸር ጀምሯል።
ክለቡ ከ14 ዓመታት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ የኦልድ ትራፎርድን ሙሉ የሜዳ ሳር በአዲስ መቀየሩን ተከትሎ፣ በቅርቡ የፋይናንስ ሪፖርቱን ይፋ ባደረገበት እና የ47 ሚሊዮን ፓውንድ ዓመታዊ ከታክስ በፊት ኪሳራ ባጋጠመበት ወቅት ይህንን ማድረጉ ተጨማሪ የገቢ ማስገኛ መንገዶችን ለመፈለግ በሚያደርገው ጥረት አካል እንደሆነ ተገልጿል።
ክለቡ ጥቂት ግራም ሳር በ125 ፓውንድ ከፍተኛ ዋጋ መሸጡን ተከትሎ ጉዳዩ በእግር ኳስ ደጋፊዎችና በማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች ዘንድ መነጋገሪያ እና የቀልድ ርዕስ ሆኗል።
Seledadotio

16 days ago