Logo
FBC
ለዓለም ምሳሌ የሆነው የኢትዮጵያ አረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር

አዲስ አበባ፣ መስከረም 13፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አነሳሽነት በ2011 ዓ.ም የተጀመረው የኢትዮጵያ አረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር የተፈጥሮ አካባቢን በመንከባከብና የደን ሽፋንን በማሳደግ ተጨባጭ ውጤት አስመዝግቧል፡፡

ዘጋርዲያን በሰራው ዘገባ ኢትዮጵያ በፈረንጆቹ 2030 ወደ 50 ቢሊየን የሚጠጉ ችግኞችን ለመትከል ያቀደችውን ታላቅ ግብና በአጭር ጊዜ ውስጥ 48 ቢሊየን የችግኝ ተከላ ስኬት በስፋት ዳሷል።

ኢትዮጵያ በወሰደችው አዎንታዊ ርምጃ የደን ሽፋኗን ከ15 ነጥብ 5 በመቶ ወደ 23 ነጥብ 6 በመቶ ማሳደግ መቻሏ በዓለም አቀፍ ደረጃ ትልቅ አድናቆትን አትርፎላታል።

ዘጋርዲያን በዘገባው የኢትዮጵያ አረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር ስኬት ምስጢር የመንግሥት ቁርጠኝነት እና የህብረተሰቡ ንቁ ተሳትፎ መሆኑን አጉልቶ አሳይቷል፡፡

ህብረተሰቡ ችግኞችን እንደራሱ ልጅ ተንከባክቦ የማሳደግ ባህል ማዳበሩን በመጥቀስ፤ ይህም ማህበራዊ እሴት እየሆነ መምጣቱ የችግኞችን የመጽደቅ መጠን ከፍ እንዳደረገው ገልጿል።

በተጨማሪም የዓለም አግሮፎረስትሪ ተቋም መረጃ እንደሚያመለክተው፤ የአረንጓዴ ዐሻራ መረሐ ግብር ከ767 ሺህ በላይ ለሚሆኑ ዜጎች በተለይም ለሴቶችና ወጣቶች የሥራ ዕድል ፈጥሯል፡፡

የኢትዮጵያን የችግኝ ማፍያ ጣቢያዎች ቁጥርም ከ40 ሺህ ወደ 121 ሺህ እንዲያድግ አድርጓል።

ይህ በዓለም አቀፍ ደረጃ ትኩረት ያገኘው የአካባቢ ጥበቃ ጥረት ኢትዮጵያ የአየር ንብረት ለውጥን ለመከላከል በሚደረገው ጥረት ውስጥ ግንባር ቀደም ሀገር እንድትሆን አስችሏታል፡፡

ለዚህም መንግሥት ለተራቆቱ መሬቶች መልሶ ማልበስ ከመደበኛ በጀቱ ከ0.5 እስከ 1 በመቶ የሚሆን በጀት መመደቡና የፍራፍሬ ችግኞችን በማስፋፋት የምግብ ዋስትናን ከደን ልማት ጋር ማጣመሩ ተጽዕኖውን አጉልቶታል።

እነዚህን ተጨባጭ የስኬት እውነታዎች መሠረት በማድረግ ኢትዮጵያ የኮፕ 32 ጉባኤን በአዲስ አበባ እንድታስተናግድ መመረጧ የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር ያስገኘው ታላቅ ዓለም አቀፍ እውቅና ማረጋገጫ መሆኑን የዘጋርዲያን ዘገባ ያመላክታል።

በአብረሃም አበራ

18 days ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.