Logo
SeledaPost
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ 29ኛውን የውጭ ምንዛሬ ጨረታ አከናወነ፤ አማካይ የመንዛሬ ተመን 160.22 ብር ደረሰ

​የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ መስከረም ዛሬ 13 ቀን 2019 ዓ.ም ባካሄደው 29ኛው የውጭ ምንዛሬ ጨረታ 125 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር ለሽያጭ አቅርቦ ነበር።

በጨረታው ተሳትፈው የቀረቡት 27ቱም ንግድ ባንኮች በሙሉ የውጭ ምንዛሬ ማግኘት የቻሉ ሲሆን፣ የቀረበው የፍላጎት መጠን 123.49 ሚሊዮን ዶላር ሆኖ ተመዝግቧል።

​በዚህም መሠረት የዕለቱ ጨረታ በ1.51 ሚሊዮን ዶላር ያነሰ ፍላጎት የቀረበበት ሆኖ ተጠናቋል።

በጨረታው የተመዘገበው ከፍተኛው የማሸነፊያ ዋጋ ለአንድ ዶላር 160.8869 ብር ሲሆን፣ ዝቅተኛው ደግሞ 158.0715 ብር ሆኗል።

የአሸናፊዎች ክብደት ያለው አማካይ የመንዛሬ ተመን  160.2297 ብር መድረሱን ብሔራዊ ባንክ አስታውቋል።

Seledadotio
Seledadotio
18 days ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.