የኮሪደር ልማት፡ የከተሞች አዲስ የልማት ገጽታ
አዲስ አበባ፣ መስከረም 13፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) የከተማ ልማት የመንገድና የሕንጻ ግንባታ ብቻ ሳይሆን፤ ለነዋሪዎች ምቹ፣ ለንግድ እድገትና ለሥራ ዕድል ፈጠራ የሚያመች ከባቢ መፍጠርንም ያካትታል።
ይህንን መርህ መነሻ በማድረግም የኮሪደር ልማት እግረኛ መንገዶችን፣ የተሽከርካሪ መንገዶችን፣ አረንጓዴ ስፍራዎችን፣ የሕዝብ መገልገያ ቦታዎችንና የከተማ መሠረተ ልማቶችን በአንድ የልማት እቅድ የሚያስተሳስር አቅጣጫ ሆኖ ተግባራዊ እየሆነ ይገኛል።
በአዲስ አበባ የተጀመሩት የኮሪደር ልማት ሥራዎችም የመንገድ ግንባታን ብቻ ያማከሉ አይደሉም።
የመንገድ ማስፋፋት፣ የእግረኛ መስመሮችን ማሻሻል፣ የፍሳሽ ማስወገጃ መስመሮችን መዘርጋትና የከተማ አረንጓዴ ልማትን በማካተት የከተማ ልማት ሥራዎች በተቀናጀ መልኩ እየተከናወኑ ነው።
ይህ የልማት አቅጣጫም በአዲስ አበባ ብቻ የተወሰነ አይደለም። የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት የ2018 ዓ.ም ሪፖርት እንደሚያሳየው፣ የተቀናጀ የኮሪደር ልማት ከአዲስ አበባ ባለፈ ከ50 በላይ ከተሞች ተስፋፍቷል።
የከተማ ልማት ውጤትም በተገነቡ መንገዶችና በተሻሻለ የከተማ ገጽታ ብቻ አይለካም። ለነዋሪዎች የሚፈጥረው ምቹ የኑሮ ከባቢ፣ ለንግድ የሚከፍተው ዕድልና የሚፈጥረው የሥራ ዕድልም የልማቱ ውጤት ናቸው።
በዓለም ባንክ መረጃ መሠረትም ከፈረንጆቹ 2018 እስከ 2024 በተከናወነው የከተማ ተቋማዊና መሠረተ ልማት ልማት ፕሮግራም ከ2 ሺህ 700 ኪሎ ሜትር በላይ መንገድ ተገንብቶ ተሻሽሏል፤ በተጨማሪም 2 ሺህ 700 ሄክታር የሚጠጋ አገልግሎት የተሟላለት መሬት ተዘጋጅቷል።
በዚህ ሂደት ከ1 ነጥብ 15 ሚሊየን በላይ የሥራ ዕድሎች የተፈጠሩ ሲሆን ከእነዚህ ውስጥ 237 ሺህ ያህሉ ቋሚ የሥራ ዕድሎች ናቸው።
መንገድና የእግረኛ መስመር፣ የውሃና የፍሳሽ አገልግሎት፣ አረንጓዴ ስፍራዎችና የሕዝብ ቦታዎች በተቀናጀ ሁኔታ ሲለሙ፣ ከተሞች ለነዋሪዎቻቸው ምቹ የኑሮ አካባቢ ከመሆን ባለፈ ለንግድ፣ ለኢንቨስትመንትና ለሥራ ዕድል ፈጠራ የተሻለ ሁኔታ ይፈጥራሉ።
በመሆኑም የተቀናጀ የኮሪደር ልማት የከተማን ገጽታ ከማሻሻል ባለፈ፣ የነዋሪዎችን የኑሮ ጥራት፣ የከተማን የኢኮኖሚ እንቅስቃሴና የወደፊት የልማት አቅም በአንድ ላይ የሚያጠናክር የከተማ ልማት አቅጣጫ ሆኖ እየተስፋፋ ነው።
በአመለወርቅ ደምሰው

17 days ago