Logo
Zehabesha
(ዘ-ሐበሻ ሕይወት) ቴይሪ ሄነሪ የኒውዮርክ መኖሪያ ቤቱን በ25 ሚሊዮን ዶላር ለገበያ አቀረበ፡፡ የቀድሞው የፈረንሳይ ብሄራዊ ቡድንና የአርሰናል ክለብ ተጨዋች ቴይሪ ሄነሪ በኒውዮርክ የሚገኘውን ‹‹ፔንት ሀውስ›› መኖሪያ ቤቱን ለሽያጭ ማቅረቡ ተዘገበ፡፡ ይህ መኖሪያ ቤት ዙሪያውን በመስታወት የተከበበና አረንጓዴ እፅዋትን ያካተተ ከርቀት በቀላሉ የሚታይ ድንቅ መኖሪያ ቤት መሆኑን ገልፍ ኒውስ ገልጿል፡፡ ተጨዋቹ ይህንን ቤት የገዛው እ.ኤ.አ በ2010 ለኒውዮርክ ሬድ ቡልስ በሚጫወትበት ወቅት መሆኑን የጠቀሰው ዘገባው የገዛውም በ15 ሚሊዮን ዶላር እንደነበር አውስቷል፡፡

በ6000 ካሬ ጫማ ላይ ያረፈውን ይህን መኖሪያ ቤት እድሳት አድርጎለት የሀድሰን ወንዝን ለማየት የሚያስችል እርከን የጨመረለት ከመሆኑም በላይ ከጣሪያው ላይ የብሩክሊንንና ዊሊያምስበርግ ድልድዮችን ማየት ይቻላል፡፡ በቤቱ ውስጥ ያሉት ግድግዳዎች ከሞላ ጎደል በመስታወት የተሰሩ በመሆናቸው ከርቀት እንዲታዩ አድርጓቸዋል፡፡ ከመሬት እስከ ጣራ የተዘረጉት እነዚህ መስኮቶች የኒውዮርክን ከተማ ገፅታ ወደክፍሉ ውስጥ የሚያስገቡ ናቸው፡፡ ሄነሪ ይህንን ድንቅ መኖሪያ ቤት ከ10 አመታት በኋላ መልሶ ለመሸጥ ማቀዱን የገለፀው ዘገባው ለንብረቱ ያወጣለት ዋጋም 25 ሚሊዮን ዶላር መሆኑን አስታውቋል፡፡ አጠቃላይ ሀብቱ 130 ሚሊዮን ዶላር የሚገመተው ይህ የእግር ኳስ ኮከብ በለንደን ውስጥም 10 ሚሊዮን ፓውንድ የሚያወጣ መኖሪያ ቤት አለው፡፡ ሄነሪ የኒውዮርክ ቤቱን ሸጦ በሲቢኤስ ስፖርት ያለውን ስራ አጠናክሮ መቀጠል እንዳቀደ ዘገዘው ጨምሮ አስረድቷል፡፡

18 days ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.