Logo
SeledaPost
በመቐለ ከተማ በፌደራል ፖሊስ አባላት ሲጠበቁ የነበሩ የፌደራል ተቋማት ያለምንም ተኩስና በህወሓት ታጣቂዎች መወሰዳቸውን አልጀዚራ ዘግቧል።
የትግራይ ኃይሎች የመቐለ አሉላ አባነጋ ዓለም አቀፍ ኤርፖርትን መቆጣጠራቸው ገልጿል።
በዛሬው ዕለት ሌሊት የተካሄደው ይህ ክስተት ያለምንም ተኩስና ግጭት የተፈጸመ በመሆኑ ምንም ዓይነት የሰውና የንብረት ጉዳት አለመድረሱ ታውቋል።

ከዚሁ አዲስ ክስተት ጋር ተያይዞ፣ ከማክሰኞ መስከረም 12 ቀን ሌሊት ጀምሮ በሰሜኑ የሀገሪቱ ክፍል ማለትም በሰቆጣ፣በአፋር(ቶንሳ)፣ በራያ ዋጃ እንዲሁም በጀመዶ ውጊያ መከፈቱን በዘገባው ተጠቅሷል።
በሰቆጣ አቅጣጫ ጠዋት የጀመረው በከባድመሳሪያ የታገዘው ተኩስ አሁንም እንደቀጠለ ነው።
የህወሓት ታጣቂዎች ወደ ዋጃ ሞርተር ተኩሰዋል።

Seledadotio
Seledadotio
18 days ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.