የትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን የቅበላ መስፈርት በተላለፉ ተቋማት ላይ ጥብቅ እገዳና የእርምጃ ማስጠንቀቂያ አስተላለፈ
የትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን የቅበላ መስፈርት ሳያሟሉ ተማሪዎችን በተቀበሉ ከፍተኛ እና ቴክኒክና ሙያ ትምህርት ተቋማት ላይ ጥብቅ ሕጋዊ እርምጃ እንደሚወስድ አስታወቀ።
በመመሪያ ቁጥር 987/2016 መሠረት መስፈርት ያላሟሉ ተማሪዎችን ያደራጁ ተቋማት አዲስ ተማሪ እንዳይቀበሉ ለሁለት ተከታታይ ዓመታት እገዳ ይጣልባቸዋል።
በተጨማሪም መስፈርቱን ያላሟሉ ተማሪዎች ወዲያውኑ ከትምህርት ገበታቸው የሚሰናበቱ ሲሆን፣ ተቋማቱ የአፈጻጸም ሪፖርታቸውን በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ ለባለሥልጣኑ ማቅረብ አለባቸው።
ሕግ ተላላፊ ሆነው የተገኙ አካላት በ20 ቀናት ውስጥ ማስተካከያ አድርገው ሪፖርት እንዲያቀርቡ የመጨረሻ የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ የተሰጣቸው ሲሆን፣ ይህንን ለማያከብሩት እስከ ሙሉ በሙሉ መዘጋት የሚደርስ እርምጃ ይወሰዳል።
እንዲሁም ማንኛውም የትምህርት ተቋም የፈቃድና የእድሳት ደብዳቤውን ለህዝብ በሚታይ ቦታ የመለጠፍ ግዴታ ተጥሎበታል።
Seledadotio

20 days ago