«ቪድዮውን እንዳጠፋው እስከ 5 ሚሊዮን ብር ወሮታ ቀርቦልኝ ነበር» - ሮዛ
በማኅበራዊ ትስስር ገጾች የተለቀቀውንና ውዝግብ ያስነሳውን የሃይማኖት አባት ፀያፍ ቪዲዮ እውነተኛነት አስመልክቶ «ተበዳይ ነኝ» ያለችው ግለሰብ ምስክርነት ሰጠች።
የግንኙነቱ መጀመር፦ አክሱም ከተማ ውስጥ ሆቴል በአስተናጋጅነት የምታገለግለው ሮዛ የተባለችው ግለሰብ፤ ከዓመት በፊት የትግራይ መንበረ ሰላም ጳጳስና ዋና ጸሐፊ ከሆኑት አቡነ አረጋዊ ጋር መተዋወቋን እና ቆይቶም ግንኙነታቸው ወደ ጾታዊ ግንኙነት ማደጉን ተናግራለች።
የቪዲዮው መቅረጽ እና የቀረበው ጉቦ፦ ጳጳሱ ጾታዊ ጥቃት እንዳደረሱባት በመግለጽ፣ መግቻ ይሆን ዘንድ በድብቅ ቪዲዮ መቅረጿን የገለጸች ሲሆን፤ ቪዲዮውን እንድታጠፋ ከጳጳሱ እስከ 5 ሚሊዮን ብር ወሮታ እንደቀረበላት ገልጻለች።
የዛቻና የደህንነት ስጋት፦ ብር ከመቀበል ይልቅ ቤተ ክርስቲያን ከዚህ ጸያፍ ተግባር እንድትላቀቅ ባላት አቋም እስከ የመግደል ሙከራ ዛቻ እንደተደረሰባትና ቪዲዮው ከቁጥጥሯ ውጭ ሆኖ መለቀቁን አብራርታለች።
ተጨማሪ ጥቆማዎች፦ ሮዛ እሷን ጨምሮ በአክሱምና ከአክሱም ውጪ የጾታዊ ጥቃት የደረሰባቸው 4 ሴቶችን እንደምታውቅና እንደምታጋልጥ አረጋግጣለች።
የአሁኑ ሁኔታ፦ ጳጳሱም ሆኑ በጉዳዩ ላይ የተሰጠ ይፋዊ ምላሽ እስካሁን የሌለ ሲሆን፤ ሮዛ በቂ የሕግ አገልግሎት እየተሰጣት በአክሱም ከተማ ትገኛለች።
Seledadotio

18 days ago