(ዘ-ሐበሻ ዜና) በርካታ ትውልደ ኢትዮጵያውያን ከሚኖሩባቸው የአሜሪካ ግዛቶች መካከል ግንባር ቀደም ከምትባለው ቨርጂኒያ ግዛት የተመረጡት ዲሞክራቱ ሴናተር ማርክ ዋርነር፣ አሜሪካ ከኢራን ጋር እያካሄደች ያለውን ጦርነት ተከትሎ በትራምፕ አስተዳደር ላይ ጠንካራ ትችት ሰነዘሩ። ሴናተሩ ትችታቸውን ያነጣጠሩት ጦርነቱ በአሜሪካውያን ቤተሰቦች ላይ በፈጠረው ከባድ የፋይናንስ ጫና እና የኑሮ ውድነት ላይ ነው።
ሴናተር ማርክ ዋርነር ባወጡት መግለጫ "ትራምፕ ከኢራን ጋር የሚያደርጉት ጦርነት 6 ሳምንታት ብቻ እንደሚወስድ ተናግረው ነበር" በማለት የፕሬዝዳንቱን የቀድሞ ቃል አስታውሰዋል።
"ነገር ግን ከ6 ወራት በላይ አልፎም ጦርነቱ አሁንም እንደተፋፋመ ነው፤" ያሉት ሴናተሩ "በዚህም ምክንያት አሜሪካውያን ለነዳጅ (ጋዝ እና ናፍጣ) ተጨማሪ 100 ቢሊዮን ዶላር፣ እንዲሁም ለመሰረታዊ የቤት ውስጥ ፍጆታዎች፣ ለምግብ ሸቀጦች እና ለቤት እዳ (Mortgages) ቢያንስ ሌላ ተጨማሪ 60 ቢሊዮን ዶላር ከኪሳቸው ለመክፈል ተገደዋል" በማለት የጦርነቱን ቀጥተኛ የኢኮኖሚ መዘዝ በቁጥሮች አጋልጠዋል።
የሴናተር ማርክ ዋርነር ትችት የትራምፕ አስተዳደር የውጭ ፖሊሲ (በተለይም የኢራኑ ጦርነት) በሀገር ውስጥ የኢኮኖሚ መረጋጋት እና በመራጩ ህዝብ የዕለት ተዕለት ኑሮ ላይ ያመጣውን ከባድ ቀውስ በጉልህ ያንጸባርቃል። በተለይም እንደ ቨርጂኒያ ባሉ በርካታ ትውልደ ኢትዮጵያውያን (የዳያስፖራው ማህበረሰብ) ሰርተው በሚኖሩባቸው ግዛቶች፣ የነዳጅ እና የመሰረታዊ ሸቀጦች እንዲሁም የቤት ክፍያ (ሞርጌጅ) በአጭር ጊዜ ውስጥ በዚህ ደረጃ መናሩ ማህበረሰቡን ምን ያህል የኢኮኖሚ አዘቅት ውስጥ እየከተተው መሆኑን ይህ መረጃ አጋልጧል። በውጭ ሀገር የሚደረግ ጦርነት የቱንም ያህል ፖለቲካዊ ምክንያት ቢሰጠውም፣ በመጨረሻው ዋጋውን የሚከፍለው መደበኛው ዜጋ መሆኑን ይህ የ160 ቢሊዮን ዶላር ተጨማሪ የኑሮ ጫና ህያው ምስክር ሆኖ ይቆማል። ይህም ከቀጣዩ ምርጫ አንጻር የትራምፕ አስተዳደርን ከፍተኛ የፖለቲካ ፈተና ውስጥ እንደሚጥለው ይጠበቃል።

18 days ago