Logo
SeledaPost
ፅዳት ሰራተኞች እያንዳንዳቸው 2,000 ብር ሺህ ብር ተቀጡ‼

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ደንብ ተላልፈው የተገኙ የመንገድ ፅዳት ሰራተኞች ላይ እርምጃ መውሰዱን አሳወቀ።

በለሚኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ 08 (ሳፋሪ አካባቢ)፣ ከመንገድ ያፀዱትን ቆሻሻ በፍሳሽ ማስወገጃ ቱቦ ውስጥ ሲደፉ በተደረገ ጥቆማ መሰረት፣ ሰራተኞቹ 2,000 ብር ተቀጥተው የጣሉትን ቆሻሻ እንዲያነሱ ተደርጓል።

ይህ እርምጃ ማንም የከተማዋን ደንብ ሲጥስ ተጠያቂ እንደሚሆን ግልፅ ማሳያ መሆኑን ባለስልጣኑ አስታውቋል።

ባለስልጣኑ፣ በብርድና በፀሀይ ሳይበገሩ ከተማችንን ንፁህ የሚያደርጉትን ታታሪ የመንገድ ፅዳት ሰራተኞች እያመሰገነ፣ ግዴለሽ የሆኑ ሰራተኞች ላይ ግን አስተማሪ ቅጣት እንደሚወስድ አሳስቧል።
መረጃው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ነው::

Seledadotio
Seledadotio
1 year ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.