ዴሞክራሲያዊ ሥርዓትን ማጎልበት ለጋራ ብልጽግና መሠረት
አዲስ አበባ፣ መስከረም 10፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) የሀገራት ጥንካሬ የሚለካው በባለፀግነት ወይም በተፈጥሮ ሀብት ብቻ ሳይሆን፣ በሕዝቦች አንድነትና ለጋራ ዓላማ ለመቆም በሚያሳዩት ቁርጠኝነትም ነው።
ኢትዮጵያ ወደ ዘላቂ ልማት የምታደርገው ጉዞ ብሔራዊ ትርክትን እና የዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታ ባህልን በጋራ ኃላፊነት እና በማይናወጥ አንድነት ላይ በመመሥረት ነው።
ብሔራዊ መግባባትን መገንባት ከፖሊሲ ቀረጻ በላይ ዴሞክራሲያዊ እሴቶችን በማኅበረሰቡ የዕለት ተለት ሕይወት ውስጥ እንደ ባህል ለማስረጽ ያስችላል።
ውይይት፣ መከባበር፣ ሰላማዊ ግንኙነት እና ማኅበራዊ ትስስር ቀላል ሀሳቦች ሳይሆኑ በተግባር የሚገለጹ ባህሎች እንዲሁም ብሔራዊ አንድነት በጽኑ መሠረት ላይ የሚያቆሙ ምሰሶዎች ናቸው።
የበለጸገ ዴሞክራሲያዊ ባህል ልዩ ልዩ አመለካከቶች በአንድ የጋራ ራዕይ ሥር እንዲሰባሰቡ ያደርጋል። ይህም ሰላማዊ፣ ጠንካራ እና የበለጸገች ሀገርን ለመገንባት መሠረት ነው።
የሕዝብን ጥቅም ለማስጠበቅ፣ መብቶችን ለማስከበር እና ማኅበራዊ ፍላጎቶችን ለማሟላት የሚሰሩ የሲቪክና የማኅበረሰብ ተቋማት አስተዋጽኦ ከፍተኛ ነው።
እነዚህ ተቋማት የሕዝብን ደህንነት በማስጠበቅ፣ እኩልነትን በማስፈን እና ማኅበራዊ ተጠያቂነትን በማጠናከር ለብሔራዊ አንድነት ደጋፊ ሆነው ያገለግላሉ።
የሲቪክ ተቋማትን አስተዋጽኦ ማጎልበት እና ሥራቸውን ከብሔራዊ ትረካው ጋር ማጣመር፣ የሀገሪቱን እድገት አሳታፊ እና የአጠቃላይ ዜጎችን ፍላጎት ያማከለ እንዲሆን ያደርጋል።
የኢትዮጵያ ሉዓላዊነት በሕዝቦቿ ጽናት እና ጀግንነት የተቃኘ የጋራ ቅርስ እንደመሆኑ ዛሬ ይህ ታሪካዊ ውርስ በእያንዳንዱ ሀገር ወዳድ ዜጋ አስተዋጽኦ ይንጸባረቃል።
ከቀደመው ጥንካሬ በመነሳት የዛሬ ዴሞክራሲያዊ ተሳትፎን ማጎልበት፣ የጋራ ምኞትን ወደሚጨበጥ ብልጽግና መለወጥ ያስችላል።
የሕዝብ አንድነትና መደጋገፍ የጋራ ንቁ እና የተባበረ ዓላማ ያላቸውን ዜጎች የመፍጠር ኃይል አለው። ኢትዮጵያን የዘላቂ ሰላም፣ ፍትሕ እና ሁለንተናዊ ብልጽግና መገኛ ማድረግ የሚቻለው በእያንዳንዳችን አስተዋጽኦ ድምር ውጤት ነው።
በምሕረት ደምሴ

20 days ago