የምክክር ድል፡ የኢትዮጵያን ሕልውና እና ብሔራዊ ጥቅም ማረጋገጥ
(የዕለቱ መልዕክት)
*******************
የኢትዮጵያ ፖለቲካዊ ታሪክ ለዘመናት ልዩነቶችን በጠመንጃ አፈሙዝ ለመፍታት በሚደረግ ተደጋጋሚ አዙሪት ውስጥ ያለፈ መሆኑ አያጠያይቅም።
ይሁን እንጂ ሀገራችን ይህን አጥፊ የፖለቲካ ባህል በመስበር በቅርቡ ያካሄደችው አካታች ሀገራዊ ምክክር፣ ልዩነቶችን በጦር ሜዳ ሳይሆን በጠረጴዛ ዙሪያ በሰለጠነ መንገድ የመፍታት ባህልን ለማዳበር አዲስ ምዕራፍና ታሪካዊ እርምጃ ነው።
ያለፉት ታሪኮቻችን ውስብስብ እና በርካታ ቂምና ቁርሾዎችን ያዘሉ ቢሆኑም መጻኢው ጊዜያችን በእነዚህ የታሪክ ስብራቶች ተተብትቦ ሊቀር አይገባም።
የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅም ለማስጠበቅ የሚደረገው ዘርፈ ብዙ የልማት፣ የዲፕሎማሲ እና ሉዓላዊነትን የማስከበር ስራ ስኬታማ ሊሆን የሚችለው በሀገራዊ መግባባት እና በይቅርታ ላይ የተመሰረተ የፖለቲካ ማዕቀፍ ሲፈጠር ነው።
የጸና ሀገረ-መንግሥት ግንባታችን እውን የሚሆነውም ሕብረ-ብሔራዊ አንድነታችንን በማክበር እንዲሁም ባህላዊ እና ዘመናዊ የእርቀ ሰላም እሴቶቻችንን በማቀናጀት የጥላቻ እና የቂም ታሪክን ለዘለቄታው መዝጋት ስንችል መሆኑን መገንዘብ ያሻል።
ብሔራዊ መግባባት፣ አንድነት እና የሀገርን ጥቅም የማስጠበቅ ኃላፊነት የጥቂት ልሂቃን ወይንም የመንግሥት ብቻ ሊሆን አይችልም፤ መሆንም የለበትም።
ከታች ጀምሮ የመላው የሀገራችንን ሕዝቦች ቀጥተኛ ተሳትፎ ባረጋገጠ መልኩ ሊገነባ የሚገባው ይህ ሂደት፣ ሀገራችንን በኢኮኖሚ፣ በዓለም አቀፍ ዲፕሎማሲ እና በጸጥታው ዘርፍ ጠንካራ አቅም ያላት ሀገር እንድትሆን ያደርጋታል።
የኢትዮጵያ ሰላምና መረጋጋት ለቀጣናውም ያለው ፋይዳ እጅግ የላቀ በመሆኑ፣ የውስጥ ጥንካሬያችን የውጭ ዲፕሎማሲያዊ አቅማችንን እና ቀጣናዊ ተሰሚነታችንን በከፍተኛ ደረጃ እንደሚያጎላው ልብ ልንል ይገባል።
ዘላቂ ሰላምን የማረጋገጥ ግብ ከዴሞክራሲ፣ ከመልካም አስተዳደር እና ከሕግ የበላይነት ጋር በእጅጉ የተቆራኘ ነው።
የፍትሕ ተቋማት ገለልተኝነት እና የዜጎች እኩልነት መረጋገጥ ለመግባባት ዲሞክራሲ መጎልበት የጀርባ አጥንቶች በመሆናቸው የበለጠ ሊጠናከሩ ይገባል።
ይህ የተጀመረው የሀገራዊ ምክክር እና የመግባባት ሂደት በቀጣይ ሀገራዊ ለውጥ እንዲያመጣ የሁሉም ዜጎችና ባለድርሻ አካላት ድጋፍ ያሻል።
በተጨማሪም ፍትሕና የሕግ የበላይነት መረጋገጥ ለዴሞክራሲ መጽናት ቅድመ ሁኔታ በመሆኑ፣ በተቋማት ግንባታ ላይ የተጀመሩ የሪፎርም ስራዎች ተጠናክረው መቀጠል አለባቸው።
ወጣቱ ትውልድም የቂም እና የጥላቻ ውርስ ተቀባይ እንዳይሆን ትምህርት ቤቶች፣ የኃይማኖት ተቋማት እና ሲቪክ ማኅበረሰቡ የሰላም፣ የይቅርታ እና አብሮ የመኖር ባህልን በማስተማር፣ በማለማመድ እና በማስረጽ ረገድ የጎላ ሚናቸውን መወጣት ይገባቸዋል።
ትናንትን በይቅርታ ተሻግረን ዛሬን በብሔራዊ መግባባት ካጸናን፣ ሕልውናዋ የተጠበቀና ሁለንተናዊ ብልጽግናዋ የተረጋገጠ ጠንካራ ኢትዮጵያን ለቀጣዩ ትውልድ ማስተላለፍ እንደምንችል ጽኑ እምነታችን ነው።
የኢቢሲ ዶትስትሪም ኤዲቶሪያል

20 days ago