(ዘ-ሐበሻ ዜና) በኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ ዕቃዎችን በማቅረብ ከሃያ ዓመታት በላይ ልምድ ያለው ሮሜል ኤሌክትሪካል ኢኪዩፕመንት፣ አዳዲስ እና ዘመናዊ የኤሌክትሪክ ምርቶችን በአዲስ አበባ ኡራኤል አካባቢ በሚገኘው የድርጅቱ ሕንፃ ይፋ አድርጓል።
ድርጅቱ ካስተዋወቃቸው አዳዲስ ምርቶች መካከል የፒያኖ ሲሪየስ ስዊቾችና ሶኬቶች፣ ማግኔቲክ እና ሊኒየር ላይቶች፣ ብሬከሮች፣ እንዲሁም የውሃ መከላከያ ያላቸው የኮርኒስ መብራቶች እና የዲስትሪቢዩሽን ቦርዶች ይገኙበታል። የድርጅቱ የግብይት እና ሽያጭ ኃላፊ በመድረኩ ላይ እንዳብራሩት፣ ሮሜል ቀደም ሲል ዕቃዎችን ከውጭ ያስገባ የነበረ ሲሆን አሁን ግን ዓለም አቀፍ መስፈርትን በጠበቀ መልኩ ሙሉ በሙሉ በአገር ውስጥ ማምረት ጀምሯል። አምራቹ ከጥሬ ዕቃ ግዢ ጀምሮ ከፍተኛ ጥንቃቄ እንደሚያደርግ የገለጹት ኃላፊው፣ የሮሜል ምርቶች በገበያው ላይ ካሉ ሌሎች ዕቃዎች አንጻር መጠነኛ የዋጋ ጭማሪ እንዳላቸው አምነው፣ ይህ የሆነው ግን "ጥራት የመጨረሻው መዳረሻችን ሳይሆን የማንደራደርበት መነሻችን ስለሆነ ነው" በማለት የጥራትን ዋጋ አስረድተዋል።

21 days ago