(ዘ-ሐበሻ ዜና) ኢትዮ ቴሌኮም፣ ንግድ ባንክ እና አዋሽ ባንክ የስቶክ ማርኬቱን መዝለቃቸውን ሰምተናል... አሁን ደግሞ ስማቸው ያልተገለጸ 11 ግዙፍ ኩባንያዎች የኢትዮጵያን የካፒታል ገበያ ሊቀላቀሉ ነው! ግን ስማቸው ለምን ምስጢር ሆነ?
የኢትዮጵያ ሠነደ ሙዓለ ንዋይ (ካፒታል) ገበያ፣ 11 አዳዲስ ኩባንያዎች ገበያውን ለመቀላቀል ያቀረቡትን ጥያቄ በመርህ ደረጃ ማጽደቁን አስታውቋል። እነዚህ ኩባንያዎች ቀደም ሲል ፈቃድ ካገኙት ስድስት ግዙፍ ተቋማት ጋር ሲደመሩ፣ በገበያው ውስጥ የሚሳተፉትን ኩባንያዎች ብዛት 18 ያደርሰዋል። የካፒታል ገበያው ሥራ አስፈጻሚ ዮዲት ካሳ እንደተናገሩት፣ ቢያንስ ስድስቱ ኩባንያዎች እስከ መጪው ታኅሳስ ወር መጨረሻ ድረስ ግብይት ይጀምራሉ ብለው ይጠብቃሉ። ነገር ግን አነጋጋሪው ጉዳይ፣ ሥራ አስፈጻሚዋ የነዚህን አዳዲስ ድርጅቶች ማንነት ከመግለጽ መቆጠባቸው ነው!
እዚህ ጋ አንድ ክሪቲካል ጥያቄ ማንሳት ግድ ይለናል! የሠነደ ሙዓለ ንዋይ ገበያ (Stock Market) የጀርባ አጥንት ምንድነው? "ግልጽነት" እና መረጃ ነጻነት አይደል! ሕዝብ ገንዘቡን አውጥቶ አክሲዮን ሊገዛባቸው የተዘጋጁ ኩባንያዎች፣ በመርህ ደረጃ ፈቃድ ካገኙ በኋላ ስማቸው ለምን እንደ ሀገር ደህንነት ምስጢር ይደበቃል? በእርግጥ ኢትዮ ቴሌኮምን የመሰሉ ተቋማት ወደ ገበያው መግባታቸው የኢትዮጵያን የፋይናንስ ሥርዓት ለማዘመን ትልቅ ርምጃ ነው። ነገር ግን የኩባንያዎቹ ማንነት መደበቁ "ኩባንያዎቹ በእውነት የፋይናንስ ኦዲት መስፈርቱን አሟልተዋል ወይስ በፖለቲካ ጓዳ እና በትውውቅ ነው እያለፉ ያሉት?" የሚል ጥርጣሬን ያጭራል። የውጭ ኢንቨስተሮችም ሆኑ የሀገር ውስጥ ገዢዎች ገበያውን እንዲያምኑት፣ መረጃዎች ከወዲሁ ገበያ ላይ መውጣት ነበረባቸው።
ዘመናዊ የኢኮኖሚ ሥርዓት በጥርጣሬ እና በድብብቆሽ አይገነባም! የሠነደ ሙዓለ ንዋይ ገበያ ስኬት የሚለካው፣ ሕዝብ በሚኖረው እምነት እና ኩባንያዎች በሚያሳዩት የፋይናንስ ግልጽነት እንጂ በማፈንገጥ አይደለም። ሕዝብ ከኪሱ ገንዘብ አውጥቶ ከመግዛቱ በፊት፣ የሚገዛውን ኩባንያ ማንነት እና የፋይናንስ ጤንነት አስቀድሞ የማወቅ ሙሉ መብት አለው!

22 days ago