Logo
SeledaPost
የኢትዮጵያ ሜትሮሎጂ ኢንስቲትዩት የክረምት ወቅት የዝናብ ትንበያ አፈፃፀም 79 በመቶ ስኬታማ መሆኑን ገለጸ፡፡

የኢትዮጵያ ሜትሮሎጂ ኢንስቲትዩት ባሳለፍነው የ 2018 ዓ.ም የክረምት ወቅት የሰጠው የአየር ጠባይ ትንበያ 79 በመቶ ትክክለኛነት ማሳየቱን ገለጿል።
 
የኢንስቲትዩቱ ምክትል ዳይሬክተር ዶክተር አሳምንነው ተሾመ እንደገለጹት፣ ኢንስቲትዩቱ ከሰኔ ወር እስከ አሁን ባለው ጊዜ ከሀገሪቱ የተለያዩ የሜትሮሎጂ ጣቢያዎች የሰበሰበው መረጃ እንደሚያመላክተው የክረምቱ ትንበያ 79 በመቶ ትክክለኛ እንደነበር ብስራት ሬድዮ ሰምቷል።

በሰሜን ምዕራብ፣ በምዕራብ እና በደቡብ ምዕራብ የሀገሪቱ ክፍሎች መደበኛ እና ከመደበኛ በላይ ዝናብ የተመዘገበ ሲሆን፤ በሰሜን ምስራቅ፣ በምስራቅ እና በመካከለኛው አካባቢዎች ደግሞ መደበኛ እና ከመደበኛ በታች የሆነ የዝናብ መጠን እና ስርጭት ተስተውሏል።

በተጨማሪም በክረምቱ ወቅት በሀገሪቱ በሚገኙ 346 አካባቢዎች በ24 ሰዓት ውስጥ ከ30 እስከ 133 ሚሊሜትር የሚደርስ እጅግ ከባድ ዝናብ ተመዝግቧል፡፡ ይህም ለግብርና እና ለተፋሰሶች የውሃ አቅም መጎልበት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ማበርከቱ ተገልጿል።

የኤልኒኖ ክስተት ሊያስከትል የሚችለውን ተጽዕኖ አስቀድሞ በማጥናት፣ የዝናብ እጥረት ሊያጋጥምባቸው ይችላል ተብለው በተለዩ 250 ወረዳዎች ላይ ጉዳቱን ለመቀነስ የሚያስችሉ የቅድመ ማስጠንቀቂያ መረጃዎች ለሚመለከታቸው አካላት እንዲደርሱ መደረጉን ኢንስቲትዩቱ አስታውቋል፡፡
Dagu
Seledadotio
Seledadotio
22 days ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.