Logo
YenetaTube
በቱርክ የግብረሰዶማውያን አክቲቪስቶች መኖሪያ ቤቶችና ባሮች ላይ በተደረገ ዘመቻ 47 ሰዎች ተያዙ።

የቱርክ ፖሊስ በግብረሰዶማውያን ማኅበረሰብ አባላትና አክቲቪስቶች ላይ ባደረገው ተከታታይ ዘመቻ 47 ሰዎች ማሰሩ ተገልጿል።

የፖሊስ እርምጃው ባለፈው ሳምንት መጨረሻ በ12 የቱርክ ግዛቶች ሲካሄድ፣ የግብረሰዶማውያን ሰዎች የሚገኙባቸውን ባሮችና የአክቲቪስቶችን መኖሪያ ቤቶች ዒላማ ማድረጉ ተዘግቧል።

ከተወሰዱት እርምጃዎች አንዱ የግብረሰዶማውያን መብቶች ተሟጋች ነኝ የሚል " Kaos GL " የተባለ ማኅበርን ዒላማ ያደረገ ነው።

የኢስታንቡል ዋና አቃቤ ሕግ ጽ/ቤት 26 ሰዎች መያዛቸውን ገልጾ፣ በዘመቻው ወቅት እጽ፣ ዲጂታል መሣሪያዎች፣ በሕገወጥ መንገድ የገባ አልኮል እና ሽጉጥ መያዙን አስታውቋል።

በተለየ መልኩ የአንካራ ዋና አቃቤ ሕግ ጽ/ቤት ከ " Kaos GL " ጋር በተያያዘ በተከፈተ ምርመራ 21 ሰዎች መያዛቸውን ገልጿል።

" Kaos GL " የተባለው ማህበር በበኩሉ 50 አክቲቪስቶች መያዛቸውን፣ ከእነዚህም ከ10 በላይ ሰዎች ከመኖሪያ ቤታቸው እንደተወሰዱ አምኗል።

ማኅበሩ ባለሥልጣናት ከግብረሰዶማውያን ድርጅቶች ጋር የተያያዙ በርካታ ድረ-ገጾችንና የማኅበራዊ ሚዲያ ገጾች መዝጋታቸውንም አስታውቋል።

ባለሥልጣናት ከ " Kaos GL " ጋር በተያያዙ በኦንላይን በሚለቀቁ ይዘቶች ላይ " አስነዋሪዎች " የሚል ክስ እንዳቀረቡ ተገልጿል።

የ" Kaos GL " X ገጽን ጨምሮ የ15 ያህል ሌሎች የግብረሰዶማውያን ድርጅቶች የX ገጾችም እንዲዘጉ መጠየቃቸው ተነግሯል።

የቱርክ መንግሥት ዘመቻውን " My Family is Safe " ወይም " ቤተሰቤ ደህና ነው " በሚል ስያሜ እያካሄደ ሲሆን ዓላማው የቤተሰብ እሴቶችን መጠበቅ እንደሆነ መንግሥት ገልጿል።

የቱርክ የፍትሕ ሚኒስትር አኪን ጉርሌክ ፥ ከግብረሰዶማውያን ጋር ከተያያዘ ከ160 በላይ ግለሰቦች፣ በርካታ ድርጅቶችና ኩባንያዎች ላይ የሕግ ሂደት መጀመሩን ገልጸዋል።

እርምጃውም ቤተሰብን መጠበቅ መሆኑን አመልክተዋል።

በቱርክ ግብረሰዶማዊነት ፅዩፍ እና እርምጃ የሚያስወስድ ህገወጥ አስነዋሪ ድርጊት ነው።

ከዚህ ቀደም የቱርክ ፕሬዚዳንት ረሲፕ ታይፕ ኤርዶጋን ግብረሰዶማውያን ሰዎችን " ጠማማዎች " በማለት በመጥራት ከወሊድ መጠን መቀነስ ጋር አያይዘዋቸው ያውቃሉ።

በቅርቡ ቱርክ ግብረሰዶማውያንን የጫነች ቅንጡ መርከብ ወደ ምድሯ እንዳይረግጥ አግዳ ማባረሯ አይዘነጋም።

@tikvahethiopia

22 days ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.