Logo
Getu Temesgen
THE GUNNERS Media የሜሪ ጆይ ኢትዮጵያን የጤና እና የዳያሊሲስ ማዕከል ጎበኘ
#ethiopia | ለአርሰናል ደጋፊዎች የተለያዩ የሚዲያ ይዘቶችን የሚያቀርበው THE GUNNERS Media፣ በአዲስ አበባ አስኮ አካባቢ የሚገኘውን ሜሪ ጆይ ኢትዮጵያ የጤና እና የዳያሊሲስ ማዕከል ጎበኘ።

በጉብኝቱ ወቅት የTHE GUNNERS Media ቡድን ሜሪ ጆይ ኢትዮጵያ በጤና ዘርፍ እያከናወነ ያለውን ሥራ እና ለህብረተሰቡ እያበረከተ ያለውን አስተዋፅኦ በመመልከት አድናቆቱን ገልጿል።

በተጨማሪም ተቋሙ እያከናወነ ያለውን ማህበራዊ ተግባርና የጤና አገልግሎት ሥራ ለሰፊው ህዝብ ለማስተዋወቅ፣ የሚዲያ መድረኮቹን በመጠቀም ድጋፍ ለማድረግ ዝግጁ መሆኑን THE GUNNERS Media ገልጿል።

በጉብኝቱ ወቅት ሁለቱ ወገኖች በወደፊት ሊኖሩ በሚችሉ የትብብር መስኮች ላይ ጥልቅ ውይይት አድርገዋል። በዚህም የትብብር ማዕቀፍ በማዘጋጀት የጋራ የመግባቢያ ሰነድ (MOU) በቅርቡ ለመፈራረም መስማማታቸው ተገልጿል።

ሜሪ ጆይ ኢትዮጵያ በበኩሉ፣ THE GUNNERS Media ለሰጠው ትኩረት፣ ማዕከሉን ለጎበኘው ቡድን እና ለወደፊት ትብብር ላሳየው ቁርጠኝነት ምስጋናውን አቅርቧል።

በሁለቱ ተቋማት መካከል የሚደረገው ትብብር የጤና እና የማህበራዊ ሥራዎችን ለህብረተሰቡ በስፋት ለማድረስ አዲስ የሚዲያ ዕድል እንደሚፈጥር ይጠበቃል።

22 days ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.