Logo
Zehabesha
(ዘ-ሐበሻ ዜና) "ከኢትዮጵያ ጋር ጦርነት ውስጥ መግባት አንፈልግም›› ሲሉ የሱዳን ሉአላዊ የሽግግር ምክር ቤት ምክትል ሊቀመንበር ገለፁ፡፡ የሱዳን ሉአላዊ የሽግግር ምክር ቤት ምክትል ሊቀመንበር ጄኔራል ማሊክ አጋር ከአዲስ አበባ በኩል ‹‹የጠላትነት አቋም›› እየጨመረ መምጣቱን ገልፀው ይሁንና ከጎረቤት አገር ኢትዮጵያ ጋር ጦርነት ውስጥ የመግባት ፍላጎት እንደሌላቸው አስታወቁ፡፡

ጄኔራሉ ሱዳን በቀጠናው ውስጥ ሰፊ የሆነ ጦርነት እንዲፈጠር የማትፈልግ መሆኑን ገልፀው የአገሪቱን የግዛት አንድነት ማስጠበቅ አስፈላጊ መሆኑን አስረድተዋል፡፡ ትላንት በካርቱም ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ ሲናገሩ ‹‹ሱዳን መንግስት፣ የመንግስት አንድነትና የተቋማት ጥምረት ያስፈልጋታል›› ያሉት አጋር የሱዳንን አንድነት ‹‹ሊጣስ የማይገባው ቀይ መስመር ነው›› ብለውታል፡፡

በአውደ ግንባር በብሉ ናይል፣ ዳርፉርና ኮርዶፋን አካባቢ የሚታየውን ሁኔታ ‹‹አበረታች›› ሲሉ የገለፁት ጄኔራሉ የሱዳን ጦርነት የሚፈታው በፖለቲካዊ ብቻ ሳይሆን በወታደራዊም መንገድ መሆኑን አስረድተዋል፡፡ አክለውም ‹‹እኛ እየተዋጋን ያለነው ከሚሊሻ ጋር ሳይሆን ከመንግስት ጋር ነው›› ያሉት ጄኔራሉ ከየትኛው መንግስት ጋር እየተዋጉ ስለመሆኑ ግን አልገለፁም፡፡

23 days ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.